የአማራ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች ልማት፣ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ እና የወሰን ጉዳዮች ናቸው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፡፡

የሕዝቡን የመልማት ፍላጎት እና ጥያቄ ለመመለስ በርካታ ፕሮጀክቶች እየተሠሩ ነው ብለዋል፡፡

ከሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጥያቄ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ ብቻ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ እና ሌሎች ክልሎችም ጥያቄ አላቸው ነው ያሉት፡፡

ደርግ የንጉሠ ነገሥቱን ሕገ መንግሥት ቀድዶ የራሱን፤ ኢሕአዴግ የደርግን ቀድዶ የራሱን ሕገ መንግሥት እንዳረቀቁ ሁሉ አሁን ያለው መንግሥት ተመሳሳይ ችግር ላለመሥራት እየሠራ ይገኛል፤ የተሻለ መፍትሔ ለማምጣትም እየሠራ ነው ብለዋል፡፡

“ሕገ መንግሥት ከመንግሥታት ጋር የሚቀየር እና የሚቀደድ መኾን የለበትም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እኛ ስንለቅ አብሮ የሚቀደድ ሕገ መንግሥት እንዳይኾን ቅድሚያ ብንመክር ይሻላል በሚል ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያዊያን ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በመውሰድ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽኑን በቅንነት ማገዝ ይገባል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው የአማራ ሕዝብ ሦስተኛው ጥያቄ የወሰን ጉዳይ መኾኑን አንስተው ችግሩ ዘላቂ ሰላምን በሚያረጋግጥ መልኩ ምላሽ እንዲያገኝ እየተሠራ መኾኑን ጠቁመዋል፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply