የአማራ ሕዝብ መብት፣ ጥቅምና ፍላጎት እንዳይከበር እንቅፋት የሚሆን አጉል ፍረጃ መቆም እንዳለበት ተጠቆመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም            አዲስ…

የአማራ ሕዝብ መብት፣ ጥቅምና ፍላጎት እንዳይከበር እንቅፋት የሚሆን አጉል ፍረጃ መቆም እንዳለበት ተጠቆመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ…

የአማራ ሕዝብ መብት፣ ጥቅምና ፍላጎት እንዳይከበር እንቅፋት የሚሆን አጉል ፍረጃ መቆም እንዳለበት ተጠቆመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመንግስት በተደረገልን ጥሪ መሰረት ወደ ብርሸለቆ ከሄድን በኋላ አታስፈልጉም መባላችን አግባብነት የጎደለው አሰራር ነው ሲሉ ምልምል ወታደሮች ቅሬታ አቅርበዋል። በቴዎድሮስ ብርጌድ የልዩ ሀይል አባልነት ተመድቦ ሲሰራ መቆየቱንና በተለያየ ምክንያት ከልዩ ሀይል ለቆ መቆየቱን የገለፀው አሸናፊ ይመር ይባላል። አሸባሪው ትሕነግ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በመከላከያ ሰራዊትና በአማራ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ከደቡብ ወሎ ዞን ተመልምሎ ለስልጠና ወደ ብርሸለቆ መምጣቱን ገልጧል። ነገር ግን ከአንድ ሳምንት ቆይታ በኋላ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም “የብ/ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ጦር ስለሆናችሁ አታስፈልጉም” ተብለናል ያለው አሸናፊ ይህን የመከፋፈል አሰራር የሚከተሉ አካላት መስተካከል እንዳለባቸው አሳስቧል። ለአማራ ሕዝብ ብለን ለመታገል በተነሳንበት በአሁኑ ሰዓት የግለሰብ ስም እየጠቀሱ በመፈረጅ አማራውን ስለምን ይጎዱታል? ሲል ቅሬታውን አቅርቧል። ሌላኛው ቅሬታ አቅራቢ መጋቢ አምሳ አለቃ ገበየሁ አድማስ ይባላል፤ በደቡብ ጎንደር ዞን በአንዳቤት ወረዳ ነዋሪ ሲሆን ከ1991 እስከ 2007 ዓ.ም በመከላከያ ሰራዊት አባልነት ማገልገሉን ተናግሯል። በ2011 ዓ.ም በመንግስት ጥሪ ከተደረገላቸው የመከላከያ ምልሶች አንዱ ሲሆን በአማራ ልዩ ሀይል ሰልጥኖም በባህር ዳርና በመተማ መስራቱን አውስቷል። ከሰሞኑም ትሕነግ በአማራ ላይ የፈፀመውን ጭፍጨፋ ተከትሎ በመቶዎች የምንቆጠር የልዩ ሀይል አባላት በተደረገልን ጥሪ መሰረት ወደ ብርሸለቆ አቅንተን ነበር ያለው መጋቢ አምሳ አለቃ ገበየሁ ይሁን እንጅ ከአንድ ሳምንት ቆይታ በኋላ ያልተገባ ፍረጃ መስጠት አታስፈልጉም በማለት በሀይል አስወጥተውናል ብሏል። ይህ አካሄድ ቅሬታ ፈጥሮብናል፤ በወረዳ ደረጃም ሰዎችን የመፈረጅ ሁኔታ በመኖሩ ያልተገባ ተፅዕኖ እየደረሰብኝ ነው ሲልም አክሏል። ለቀረበው ቅሬታ ምላሽ እንዲሰጡበት በሚል የአማራ ክልል የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር መለስን ያነጋገርን ሲሆን ኮማንደሩ በምላሻቸው ጉዳዩ ከዲሲፒሊን ጉድለት ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ አስተባብለዋል። አያይዘውም በዛሬው እለት ከዲሲፒሊን ጉድለት ጋር በተያያዘ 14 እንዲወጡ መደረጉን አውስተው በዚህም እንደሚቀጥሉበት አረጋግጠዋል። ኮሚሽኑ በሰጠን አቅጣጫና ውሳኔ መሰረት በቦርድ፣በጦረታና በዲሲፒሊን ጉድለት የወጡትን አንቀበልም ነው ያሉት ኮማንደሩ። በብር ሸለቆ ማሰልጠኛ ጣቢያ የሚሰሩትን ኮማንደር መንገሻን በእጅ ስልካቸው ለማግኘት በሚል በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት የሚጠራ ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ምላሻቸውን ለማካተት አልተቻለም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply