“የአማራ ሕዝብ መንታ ትግል የኢትዮጵያን ሕልውና ማስጠበቅና በማንነቱ ላይ የተጋረጡ ፈተናዎችን አስወግዶ ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በሰላም መኖር ነው”  አቶ ጣሂር ሙሐመድ የአማራ ብሔራዊ ን…

“የአማራ ሕዝብ መንታ ትግል የኢትዮጵያን ሕልውና ማስጠበቅና በማንነቱ ላይ የተጋረጡ ፈተናዎችን አስወግዶ ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በሰላም መኖር ነው” አቶ ጣሂር ሙሐመድ የአማራ ብሔራዊ ን…

“የአማራ ሕዝብ መንታ ትግል የኢትዮጵያን ሕልውና ማስጠበቅና በማንነቱ ላይ የተጋረጡ ፈተናዎችን አስወግዶ ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በሰላም መኖር ነው” አቶ ጣሂር ሙሐመድ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ… ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከድርጅቱ የወረዳና የዞን አመራሮች ጋር ለሁለት ቀናት የሚቆይ ውይይት ዛሬ በባሕር ዳር እያካሔደ ነው፡፡ የውይይቱ ዓላማ አብን ከቅድመ ምሥረታ እስካሁን የተጓዘባቸውን የፖለቲካ ትግሎችን መገምገም፣ በሂደቱ የነበሩ ችግሮችን ለይቶ መፍትሔ ማስቀመጥና በቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ መግባባት መፍጠር ነው፡፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጣሒር ሙሐመድ በውይይቱ በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ የኃይል አሠላለፍ ምን እንደሚመስልና ብሔርተኝነቱ ሊያሳካ የሚፈልጋቸው ሂደቶች ምን መምሰል እንለባቸው ይነሳሉ ብለዋል፡፡ ድርጅታዊ ርዕዮተ ዓለምን አስመልክቶ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ የሚያሳልፋቸውን ውሳኔዎች የዞንና የወረዳ የድርጅት ኃላፊዎች በትክክል ስለመረዳታቸው በማየትም ቀጣይ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ምክክር ይደረጋል ነው ያሉት፡፡ “የአማራ ሕዝብ መንታ ትግል የኢትዮጵያን ሕልውና ማስጠበቅና በማንነቱ ላይ የተጋረጡ ፈተናዎችን አስወግዶ ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በጋራ መኖር ነው” ያሉት አቶ ጣሂር የውይይቱ ትኩረትም ይህን ማሳካት በሚያስችል የድርጅቱ ርዕዮተ ዓለማዊ ጉዳዮች ላይ ግልጸኝነት መፍጠር እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡ ውይይቱ በማዕከላዊ ኮሚቴ አማካኝነት የሚሠሩ የነባራዊ ሁኔታና የፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ትንተናዎችን አስመልክቶ የታችኛው መዋቅር በምን መልኩ እንደሚገነዘበው ለመረዳትም ይረዳል ብለዋል፡፡ ውይይቱ ሲጠናቀቅ ርዕዮተ ዓለማዊ ጉዳዮችን፣ የፖለቲካ የኃይል አሰላለፎችንና የነባራዊ ሁኔታ ትንተናን አስመልክቶ ለቀሪ አባላትና የድርጅቱ ደጋፊዎች ግልጽነት የመፍጠር ሥራው ይቀጥላል ተብሏል፡፡ እስካሁን በነበሩ የድርጅቱ የትግል ሂደቶች የነበሩ ክፍተቶችን በመለየትም መፍትሔ ይሰጣል፤ ይህም ሰላምና ደህንነትን በማረጋገጥ ቀጣይ ለሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ መዋቅሩን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚረዳ ነው አቶ ጣሂር የተናገሩት፡፡ ለዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ አሰቃቂ ግድያ፣ ማፈናቀልና ንብረት የማውደም ወንጀሎች እየደረሱ ነበር፤ ብሔር ተኮር ጥቃቶቹ አሁንም ማባሪያ አላገኙም፡፡ እነዚህን ለማስቆም አብን የረጅምና የአጭር ጊዜ የትግል ስልት ይከተላል ብለዋል፡፡ መንግሥት የሰላም ማስከበርና የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አብን ውይይትና ድርድር በማድረግ የድርሻውን ይወጣልም ብለዋል፡፡ የራሱን የፖለቲካ አቅጣጫ በማስቀመጥ ሕዝቡ ራሱን አደራጅቶ እንዲጠብቅም ይሠራል ነው ያሉት፡፡ አቶ ጣሂር እንዳሉት አብን በማንነት ላይ የሚፈፀም ሁለንተናዊ ጥቃት በዘላቂነት እንዲቆም መዋቅራዊና ሥርዓታዊ ማሻሻያ እንዲኖር በጽናት ይታገላል፤ ለዚህም የትህነግ መደምሰስ ትልቅ ሚና አለው፤ የትህነግ ሀሳብ ገዝተው የሚሠሩ አካላት ተግባራቸውን ለማስቀረት በትኩረት እንደሚሠራ አመላክተዋል ሲል አብመድ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply