የአማራ ሚዲያ ማዕከል በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት ተገኝቶ በእስር ቤቱ ውስጥ ተፈጥሯል ስለተባለው ችግር ኃላፊዎችን በማግኘት ለማጣራት ያደረገው ሙከራ ክልከላ ገጠመው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

የአማራ ሚዲያ ማዕከል በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት ተገኝቶ በእስር ቤቱ ውስጥ ተፈጥሯል ስለተባለው ችግር ኃላፊዎችን በማግኘት ለማጣራት ያደረገው ሙከራ ክልከላ ገጠመው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

የአማራ ሚዲያ ማዕከል በጎንደር አንገረብ ማ/ቤት ተገኝቶ በእስር ቤቱ ውስጥ ተፈጥሯል ስለተባለው ችግር ኃላፊዎችን በማግኘት ለማጣራት ያደረገው ሙከራ ክልከላ ገጠመው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ትናንት ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም በግቢው ውስጥ ተከስቷል ስለተባለው የፀጥታ እና ይታያሉ ስለተባሉት አስተዳደራዊ ችግሮችን በተመለከተ እስረኞችን ብሎም የማ/ቤቱን ኃላፊ ለማነጋገር በሚል ወደ አንገረብ ማ/ቤት በማቅናት ያደረገው ሙከራ ክልከላ ገጥሞታል። የማ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ መሆናቸውን የገለፁት አመራር በትናንትናው እለት በእስረኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት የቤተሰብ ግንኙነት ለጊዜው መታገዱን በመግለፅ አይቻልም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ተባበሩት የሚል ደብዳቤ ከተቋምህ አፅፈህ አልመጣህም በሚል እና ሌሎች ሊቀሩ የሚገባቸው ጎታች ቢሮክራሲያዊ አሰራሮችን እንደ መልካም ነገር በማሰቀጠል ከእስረኞች፣ ከማ/ቤቱ የፖሊስ አባላት እና ከእስረኛ ቤተሰቦች ጭምር ለተነሱ ቅሬታዎች ምላሽ ለመስጠት ያልፈቀዱት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ከዋና አመራሩ ጋር እንዳናገኝ አድርገዋል። እነማንን ነው የምትጠይቁ በሚል ስልካችንና መታወቂያ ተቀብለው ለሰዓታት የቆዩት፣ የአደራ እስረኛውን ፋኖ አርበኛ ብርሃኑ ነጋን፣የፋኖ መሪ ሰለሞን አጠናውን፣ፋኖ አለልኝ ገብሩ እና ሎሎችን እስረኞችን ለመጠየቅ የመጣን መሆኑን ከሰሙ በኋለ ግንኙነት ተከልክሏል ብለዋል። የአንገረብ ማ/ቤት ኃላፊ ለሆኑት ለኮማንደር ይሄነውም ከአማራ ሚዲያ ማዕከል የመጣ ባለሙያ እንደሚፈልጋቸው በስልክ ተነግሯቸዋል። ስብሰባ ላይ ነኝ ይጠብቅ ብለዋል በሚል ከ9 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት ብንጠብቃቸውም ሊመጡ እና ሊፈቅዱ አልቻሉም፤ በወቅቱ በእጅ ስልካቸው ላይ ስንደውልም አላነሱልንም፤ ምሽት ላይ ደግመን ስንደውል በማንሳትም ከስብሰባ ስለወጣሁ ደክሞኛል በማለት ቅሬታዎችን ከመስማትና ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ክልከላ የገጠመው የአማራ ሚዲያ ማዕከልም ለማጣራት እንደሞከረው በግቢው ውስጥ በታራሚዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በአካሉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት እስረኛ ስለመኖሩና በዚህም ምክንያት የቤተሰብ ግንኙነት ክልከላ ስለመደረጉ ለማወቅ ችሏል። ይህ ክልከላም በቤተሰብ ላይ ቅሬታ የፈጠረ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከተለያዩ የእስረኛ ቤተሰቦች እና ከፖሊስ አባላት ያገኘው መረጃ እንዳመለከተው በአንገረብ ማ/ቤት ከፍተኛ የሆነ የውሃ አቅርቦት ችግር አለ። አባላትም ደመዛቸው ዝቅተኛ በመሆኑ በኑሮ እየተፈተኑ መሆኑንና አስታዋሽ ያጡ መሆናቸውን የሰማው አሚማ ከዝውውር ጋር ተያይዞም ችግር ስለመኖሩ ጥቆማ ደርሶታል። ለጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እያገኙ ባለመሆኑም በቅርቡ ሁለት አባላት ከስራ መልቀቃቸውን ነው የደረሰን መረጃ ያመለከተው። የአማራ ሚዲያ ማዕከልም እስረኞችንና የማ/ቤት ኃላፊን ለማነጋገር በሚል ከህጉ አልፎ እስከ ልመና የደረሰ ቢሆንም ትብብር በመነፈጉ ከ3 ሰዓታት ጥበቃ በኋላ ሳይሳካለት ተመልሷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply