You are currently viewing የአማራ ማህበር በአሜሪካ፣ በኦሮሚያ ክልል  ኪረሙ፣ አሙሩ፣ ሆሮ፣ አቤ ዶንጎሮ እና ጃርዴጋ ጃርቴ በተባሉ አምስት ወረዳዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በአካባቢው መስ…

የአማራ ማህበር በአሜሪካ፣ በኦሮሚያ ክልል ኪረሙ፣ አሙሩ፣ ሆሮ፣ አቤ ዶንጎሮ እና ጃርዴጋ ጃርቴ በተባሉ አምስት ወረዳዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በአካባቢው መስ…

የአማራ ማህበር በአሜሪካ፣ በኦሮሚያ ክልል ኪረሙ፣ አሙሩ፣ ሆሮ፣ አቤ ዶንጎሮ እና ጃርዴጋ ጃርቴ በተባሉ አምስት ወረዳዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በአካባቢው መስተዳድር አካላት ጥምረት ጥቃት ሊፈጸምባቸው እንደሚችል አመላከተ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ኪረሙ፣ አሙሩ፣ ሆሮ፣ አቤ ዶንጎሮ እና ጃርዴጋ ጃርቴ በተባሉ አምስት ወረዳዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በአካባቢው መስተዳድር አካላት ጥምረት ሊጠቁ እንደሚችል ያመላከተው የአማራ ማህበር በአሜሪካ ይህን ያለው የነዋሪዎችን የጭንቀት ጥሪ ዋቢ አድርጎ ስለመሆኑ ጠቁሟል። መስከረም 6 ቀን 2022 እኤአ የተደረገውን ስብሰባ ተከትሎ አማራዎችን ለማጥቃት የአካባቢው ባለስልጣናት ከኦሮሞ ነጻነት ጦር (OLA) ጋር ለመተባበር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል። ይህን የካድሪዎችን ውሳኔ ተከትሎ የጭንቀት እና የድረሱልን ጥሪ ከአካባቢው ነዋሪዎች ለአማራ ማህበር በአሜሪካ እየደረሰው ስለመሆኑ ጠቁሟል። በኪረሙ እና ጃርዴጋ ጃርቴ አዋሳኝ መንደር መስከረም 7 ቀን 2022 እኤአ አምስት አማሮች መገደላቸውን አውስቷል። በመጨረሻም ማህበሩ በኦሮሚያ ላይ ሌላ መጠነ ሰፊ የአማራውን እልቂት ለመከላከል በኦነግ እና በአካባቢው ባለስልጣናት ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ ሰዎች እርምጃ እንዲወስዱ እናሳስባለን ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply