You are currently viewing የአማራ ማህበር በአሜሪካ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ያሰማራው ልዩ ኃይል በጃርዴጋ አግቷቸው ከነበሩት አማራዎች አምስቱ ተገድለው መገኘታቸውን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ታህሳስ…

የአማራ ማህበር በአሜሪካ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ያሰማራው ልዩ ኃይል በጃርዴጋ አግቷቸው ከነበሩት አማራዎች አምስቱ ተገድለው መገኘታቸውን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ…

የአማራ ማህበር በአሜሪካ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ያሰማራው ልዩ ኃይል በጃርዴጋ አግቷቸው ከነበሩት አማራዎች አምስቱ ተገድለው መገኘታቸውን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 13 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ጃርዴጋ እና አካባቢው ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 1/2015 በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ታግተው ደብዛቸው ከጠፉት በርካታ አማራዎች መካከል 5 የሚሆኑት ተገድለው እና በእሳት ተቃጥለው መገኘታቸውን የአማራ ማህበር በአሜሪካ አስታውቋል። የሟቾቹ የተቃጠለ አጥንት ወድቆ የተገኘውም ታህሳስ ባሳለፍነው ሰኞ እና ማክሰኞ ታህሳስ 10 እና 11/2015 መሆኑ ተገልጧል። ከአስከፊ የእገታ ቆይታ በኋላ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጃርዴጋ ላይ ተገድለው የተገኙትም:_ 1) ኢብራሂም በድሩ፣ 2) ሙሉጌታ ጌታቸው፣ 3) ሞላ በላይ፣ 4) ኡመር አዳም እና 5) ከማል አለባቸው እንደሚባሉ በሪፖርቱ አመላክቷል። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከተጎጅ ቤተሰቦች ሲደወልለት ደህና ናቸው፣ ህክምና ላይ ናቸው፣ ጉዳያቸው በህግ ታይቶ በቅርብ ይለቀቃሉ ይላቸው እንደነበር ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply