የአማራ ማህበር በዩናይትድ ኪንግደም 400 መለስተኛ ብርድ ልብሶችን በ80 ሺህ ብር ወጪ እንዲገዙ በማድረግ ከመተከል ለተፈናቀሉ ወገኖች አበረከተ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 30 ቀን…

የአማራ ማህበር በዩናይትድ ኪንግደም 400 መለስተኛ ብርድ ልብሶችን በ80 ሺህ ብር ወጪ እንዲገዙ በማድረግ ከመተከል ለተፈናቀሉ ወገኖች አበረከተ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ማህበር በዩናይትድ ኪንግደም በእነ ሸፈቀ አደም መሀመድ አስተባባሪነት 400 መለስተኛ ብርድ ልብሶችን በ80 ሺህ ብር እንዲገዛ በማድረግ በመተከል ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን በእነ ምስጋናው ዘ_ግዮን በኩል ማድረሱ ታውቋል። ማህበሩ በተለያዩ ጊዜያት ማህበራዊ ተሳትፎ በማድረግ በኩል የድርሻውን ሲያበረክት መቆየቱ ተጠቅሷል። እርዳታ የተደረገላቸው ተፈናቃዮችም ከመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ሙዘን ከሚባል ቀበሌ ህዳር 6 ቀን 2013 ዓ.ም ከተፈፀመው ጭፍጨፋ አምልጠው ከቻግኒ ከተማ በግምት 15_ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይማሊ ከሚባል ቦታ ለተጠለሉት መሆኑን ድጋፉን ያደረሰው ምስጋናው ዘ_ግዮን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል። ተፈናቃዮቹ እስካሁን ምንም እርዳታ እንዳልደረሳቸው ስለመናገራቸውም ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply