You are currently viewing የአማራ ማህበር በዩጋንዳ በምዕራብ  ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ለተጨፈጨፉ ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ፤ አማራው የዘር ማጥፋት ወንጀልን በማስቆም ሕልውናውን ለማስከበር የሚያደርገው ትግ…

የአማራ ማህበር በዩጋንዳ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ለተጨፈጨፉ ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ፤ አማራው የዘር ማጥፋት ወንጀልን በማስቆም ሕልውናውን ለማስከበር የሚያደርገው ትግ…

የአማራ ማህበር በዩጋንዳ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ለተጨፈጨፉ ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ፤ አማራው የዘር ማጥፋት ወንጀልን በማስቆም ሕልውናውን ለማስከበር የሚያደርገው ትግልም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ማህበር በዩጋንዳ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በማንነታቸው ብቻ በጅምላ ለተጨፈጨፉ ከ1,500 በላይ ይደርሳሉ ሲል ለገለጻቸው አማራዎች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጧል። ማህበሩ በመግለጫው በጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ከ3 ቀን ህጻን ጀምሮ እስከ 80 ዓመት የሆናቸው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና እናቶች ጭምር በአማራነታቸው ብቻ በጅምላ መጨፍጨፋቸውን ገልጧል። የዘር ማጽዳት ተግባሩም ከአማራ ነጻ የሆነች ኦሮሚያን ለመገንባት ካላቸው አላማ ነው ያለው የአማራ ማህበር በዩጋንዳ ይህም የእነ ሽመልስ አብዲሳ እና አብይ አህመድ የረዥም ጊዜ እቅድ ነው ብሏል። “የአማራን ሞት ከውሻ ሞት አሳንሰው የሚያዩ አካላት አሉ” ያለው የአማራ ማህበር በዩጋንዳ ለዚህ መድሃኒቱ የተጀመረውን የህልውና ትግል አጠናክሮ መቀጠል መሆኑን ጠቁሟል። ብአዴን ዛሬም እንደ ትናንቱ የአማራ ገዳዮች ተባባሪ ሆኖ መቀጠሉንም ገልጧል። የአማራው የጅምላ ፍጅት ለብሄራዊ ሀዘን ቀን ለማወጅ እንኳን ያልበቃው በሞታችን ፖለቲካ የሚሰራብን ህዝብ ሆነናል ሲል ቁጭቱን ገልጧል። እንደ አማራ ለዚህ ሁሉ ሁለንተናዊ ችግር የተዳረግነው መደራጀት ባለመቻላችን ነው ብሏል። በ1,500 አማራዎች እልቂት ከእኛ ይልቅ አሜሪካዊያን መጮሃቸውን የገለጸው ማህበሩ የትኛው የአማራ ባለስልጣን ሞታችንን በስሙ ጠርቶ አወገዘ? ፣ የትኛው የአማራ ባለስልጣን በወገኖቹ ሞት ተሳቆ ስልጣኑን ለቀቀ? ሲል ጠይቋል። “ፓርላማው ተሳለቀብን፤ ብአዴናዊያን ለፓርላማው አጨበጨቡ፤ በእነ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ላይ አፈ ጉባኤው አጓራ፤ በሞታችን ላይ ሌላ ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ ይህንንም ታሪክ ይመዘግባል፤ ብአዴናዊያንም ቁጭ ብለዋል” ሲል ፓርላማ ላይ የነበረውን ሁኔታ አውስቷል። ባለፉት 4 ዓመታት የአብይ አህመድ የስልጣን ዘመን ከ1 ሚሊዮን አማራ በላይ ከመተከል እስከ ወለጋ አልቋል፤ በጅምላ ተጨፍጭፏል፤ ተረሽኗል ሲል የገለጸው የአማራ ማህበር በዩጋንዳ ከ5 ሚሊዮን በላይ አማራም ቤት ንብረቱን ጥሎ ተፈናቅሎ በየድንኳኑ፣ በየጫካውም መበተኑን ጠቁሟል። መንግስት ይህን የጅምላ ፍጅት ለማስቆም ስራ እየተሰራ ባለመሆኑ አማራን ከኦሮሚያ የማጽዳት እና ታላቋን የኦሮሚያ ሪፐብሊክ የመገንባት እቅዳቸው በፍጥነት እየተካሄደ መሆኑን በመግለጫው አካቷል። አማራ ከራሱ እርስት ከመተከል የተገፋበት ዋነኛ ምክንያትም አማራን ከአባይ ግድብ የባለቤትነት ድርሻ እንዳይኖረው ለማድረግና በሂደትም የኦሮምኛ ቋንቋ በክልሉ እየተሰጠበት ያለውን የቤንሻንጉል ክልልን ወደ ኦሮሚያ ሪፐብሊክ ለማጠቃለል የታለመ ስለመሆኑ አስምሯል። አማራው ዘሩ እንደ መካከለኛው ምስራቅ የኩርድ ህዝብ እንዳይጠፋ ከፈለገ እና ከፈለግን የሚከተሉትን አጀንዳዎች በመስዋዕትነት ማስፈጸም አለበት፤ አለብን:_ 1) የአማራ መሰረታዊ ጠላቱ ህገ መንግስቱ መሆኑን አውቆ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን አማራውን ጭምር ያካተተ ህገ መንግስት ማዘጋጀት አለበት፤ አለብንም። 2) የአማራ የጅምላ ጭፍጨፋ በመንግስት እውቅና እንዲያገኝና ለተሰው አማራዎች አዲስ አበባ ላይ የሰማዕታት ሀውልት እንዲቆምላቸው መታገል አለብን፣ 3) በአማራ ላይ የሚካሄደውን የጅምላ ጭፍጨፋን የሚያስቆም አስቸኳይ አዋጅ እንዲወጣ መታገል አለብን፣ 4) ለሕልውናዬ ስል እምቢ አልገዛም የሚለው የአማራው ትግል እንዲቀጥል ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ፣ 5) በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚኖሩ የአማራ ምሁራን በመርህ ደረጃ ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዲፈጥሩ ጫና ማድረግ ያስፈልጋል። 6) ማንኛውም አማራ በአማራ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በተመለከተ ከጎረቤቱ ጀምሮ ማስረዳት አለበት፣ 7) በመጨረሻም የአማራ ማህበር በዩጋንዳ የአማራው ትግል መቆም ያለበት የተዘረዘሩትን ሲያሳካ እና አብይ አህመድ፣ ደመቀ መኮንን፣ ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጻሚ እና አስፈጻሚዎች በፍርድ አደባባይ ሲቀርቡ መሆን አለበት ብሎ እንደሚያምንም አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply