የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/በአማራ ህዝብ ላይ እያጋጠሙ ባሉ ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ለዞንና ወረዳ አመራሮች ሰጠ፡፡ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 16/2013ዓ.ም ባህርዳር…

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/በአማራ ህዝብ ላይ እያጋጠሙ ባሉ ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ለዞንና ወረዳ አመራሮች ሰጠ፡፡ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 16/2013ዓ.ም ባህርዳር /// ጥቅምት 15/2013 ዓ.ም ለሁለተኛ ዙር በባህርዳር ከተማ በተሰጠው ስልጠና ላይ ባለፉት 30 አመታት በአማራ ላይ የተሰጡ የውሸት ትርክቶችን በተመለከተ፤ንቅናቄው ቀጣዩን ሀገራዊ ምርጫ በውጤታማነት ለማጠናቀቅ የታችኛው አመራር ሚናን በተመለከተ ስልጠናውን አካሂዷል፡፡ የአብን የምዕራብ ጎጃም ዞን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ደናሁን ቤዛ ለአሻራ ሚዲያ እንደገለፁት ከስልጠናው በተጨማሪ ጥቅምት 18 እና 20 ሊካሄድ ስለታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ ውይይት ተደርጓል፡፡ ህዝቡ በሰልፉ ላይ ተገኝቶ በአማራ ወገኖቹ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ እና በደል እንዲያወግዝም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አብን በአማራ ክልልና በአዲስ አበባ የተጠሩት የተቃውሞ ሰልፎች ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆኑና ሊከተሉ የሚችሉ አላስፈላጊ እረብሻዎችንና ጥቃቶችን ለማስቀረት ሕዝቡ የራሱን ደኅንነት በንቃት እንዲጠብቅ ማሳሰቡ የሚታወስ ነው፡፡ ዘጋቢ፦በረከት የሽዋስ

Source: Link to the Post

Leave a Reply