የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን አባላትና አመራሮች የሚወዳደሩበትን አካባቢ ይፋ በማድረግ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን እያከናወኑ ነው።   አሻራ ሚዲያ የካቲት 27/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር ለአማራ…

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን አባላትና አመራሮች የሚወዳደሩበትን አካባቢ ይፋ በማድረግ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን እያከናወኑ ነው። አሻራ ሚዲያ የካቲት 27/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር ለአማራ…

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን አባላትና አመራሮች የሚወዳደሩበትን አካባቢ ይፋ በማድረግ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን እያከናወኑ ነው። አሻራ ሚዲያ የካቲት 27/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር ለአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን ከሚወዳደሩት መካከል የቀድሞው የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔን ጨምሮ የፓርቲው ም/ሊቀመንበር አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም፣ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊው አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ የቀድሞው የሳተናው የድሬድዋ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ሲሳይ አየለ፣በምርጫ ቦርድ እንዳይወዳደር የተደረገው የሐረር ፍትህና ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራር ሄኖክ ሀይሉ እና ሌሎችም የትና ለማን እንደሚወዳደሩ ታውቋል። በዚህም መሰረት፡- – ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ባህር ዳር ከተማ፣ የባህር ዳርንና የአማራን ህዝብ ወክየ በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አቅራቢነት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት ለመወዳደር መመዝገቤን ሳበስር በታላቅ ትህትና፣ ክብርና ኩራት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሰረት የባህር ዳር ዩኑቨርስቲ መምህርና የቀድሞው የአብን ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ በባህር ዳር ይወዳደራሉ፡፡ – ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ ፡- እነሆ በትውልድ መንደሬ ራያ ቆቦ ተገኝቸ የእጩ ምዝገባ ፈፅሜአለሁ፡፡ ዛሬም አንድ የእፎይታ ቀናችን ሆኖ ውሏል። ለእፎይታችን ምክንያት ደግሞ ወዲህ ነው….በቤኒሻንጉል፣ ኦሮምያ፣ ሀረሪ፣ በድሬዳዋ፣ በደቡብ፣ በአዲስ አበባ በእቅዳችን መሠረት ብርቅየ የአማራ ልጆችን በቻልነው ሁሉ አሠልፈን ለማስመዝገብ ችለናል። ይህ በራሱ ብቻውን ትርጉሙ ከፍ ያለ ነው። “የመጀመሪያው አማራዊ ምርጫ” ማለታችንም ለዚሁ ነው ብለዋል ። ፕሮፌሰሩ በራያ ቆቦ እንደሚወዳደሩ ገልጸዋል፡፡ – ክርስቲያን ታደለ፡- ቋሪትን ወክለው እንደሚወዳደሩ ተሰምቷል፡፡ – ጣሂር ሙሀመድ፡- የዘንድሮውን ስድስተኛ ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ ተወልጄ ባደግኩባት ከተማየ ‹እንፍራንዝ› እወዳደራለሁ ብሏል ። ጨምሮም በርትቼ እንድሰራ እና ትልቅ ህልም እንዲኖረኝ ስትደክሙ ለኖራችሁ አብሮ አደጎቼ እና ታላቆቼ በዚህ አጋጣሚ ምስጋናየ ይድረሳችሁ ። በድህነት ተቸግረው ያስተማሩን እና ለቁም ነገር እንድንበቃ የደከሙ ቤተሰቦቻችን ዛሬም ድረስ ኑሯቸው ሳይቀየር በችግር ለሚኖሩ ወገኖቻችን የምንደርስበት ጊዜው አሁን ነው ፡፡ – የሱፍ ኢብራሂም፡- ወሎ የሀሳብ ብዝሀነትና መከባበር ያለበት ቀጠና ነው ፡፡ ወሎ በኢትዬጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አቅጣጫ ቀያሪ ስምሪቶች የሚደረጉበት ቀጠና ነው። በርግጥ አጠቃላይ የፖለቲካ ጥልፍልፎሽ የሚካሄድበት መልክአምድርም ነው። አካባቢው ላይ በርካታ ፍላጎቶች ልዩ ትኩረት አድርገው ቢተራመሱ የሚገርም አይደለም። በሁሉም ሀሳብ ስምምነት ቢኖረንም ባይኖረንም፣ ፊትአውራሪ አመደ ለማን፣ ነገደ ጎበዜን፣ ዋለልኝ መኮነንን፣ ጥላሁን ግዛውን የመሳሰሉ ሰዎች ከወጡበት ማህበረሰብ ውስጥ ስላደግኩ የማይመስለኝን ነገር ለመጋፈጥ ወደኋላ የምልበት ምክንያት ስለሌለ የወያኔ አፈና የመጨረሻ ደረጃው ላይ በነበረበት ወቅት የማምንበትን ትግል መስርቸና አደራጅቼ ከጓደኞቸ ጋር ለዚህ በቅቻለሁ ብለዋል፡፡ ምዝገባውን ትላንት የፈፀምኩ ቢሆንም ነገሮች በደስታ ስለተምታቱብኝ ምንም ነገር ሳልፅፍ ቆይቻለሁ። የዚህ ህዝብ ወኪል መሆን በራሱ ከማናቸውም ስልጣን በላይ ነው ያሉት የሱፍ ኢብራሂም ወሎ ላይ እንደሚወዳደሩ ተናግረዋል፡፡ – ጋሻው መርሻ፡- በዚህ ሁለት ቀን በጌምድር እስቴ ነኝ። መብራት የሚባል ነገር የለም። በቀን ለተወሰነ ደቂቃ ብልጭ ድርግም ይላል። ይቺን ሁለት መሥመር የጻፍኳት በጀኔሬተር ቻርጅ አድርጌ 5% ባትሪ በማግኘቴ ነው። አምፖል የመመረጥ እድሏ ያገልግሎቷን ያክል ይሆናል። ምርጫችሁ ሰዓት ይሁን… በማለት በበጌምድር እስቴ እንደሚወዳደሩ ተናግረዋል፡፡ – ዶ/ር ቴዎድሮስ ሀይለማርያም ፡- አዲስ አበባን ወክለው ይወዳደራሉ፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply