የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የሸዋሮቢት ከተማና የቀወት ወረዳ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ለጽ/ቤቱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትና ለቀበሌ አደረጃጀቶች ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ። አማራ ሚዲ…

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የሸዋሮቢት ከተማና የቀወት ወረዳ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ለጽ/ቤቱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትና ለቀበሌ አደረጃጀቶች ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ። አማራ ሚዲ…

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የሸዋሮቢት ከተማና የቀወት ወረዳ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ለጽ/ቤቱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትና ለቀበሌ አደረጃጀቶች ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የሸዋሮቢት ከተማና የቀወት ወረዳ ማስተባበሪያ ጽህፈት በ “ርእዮተዓለም፣ ወቅታዊ ፖለቲካ፣ የትግል ስትራቴጂና ቅድመ-ምርጫ ወትሮዝግጁነት” በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ስልጠና መስጠቱን አስታውቋል። በስልጠውም የአማራ ህዝብ መሰረታዊ የሆኑ የትግል እንቅስቃሴዎች የተዳሰሱበትና የትግሉ አጠቃላይ ሂደቶች የአማራ ህዝብን በሚመጥን መልኩ እንደሚንቀሳስ ተገልጧል። መሬት ላይ የወረደ የትግል እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግና በቀጣይ ለሚኖር ድርጅታዊ እንቅስቃሴ በቂ ግንዛቤ በመጨበጥ ለምናደርገው የአማራ ህዝብ ህልውና የማስቀጠልና ሀገራዊ አንድነትን የማስጠበቅ መንታ ትግል በሙሉ አቅም በመንቀሳቀስ ፍትህ ነጻነትና እኩልነት የሰፈነባት ሀገር ለመገንባት በሙሉ አቅም መንቀሳቀስ በሚያስችል ደረጃ መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል። በቀጣይም ትግሉን ማቀጣጠልና የማህበረሰቡን የፖለቲካ ንቃተ ህሊና ማሳደግና አደረጃጀቱን ማጠናከር ለነገ የማይባል ተግባር መሆኑን በመተማመንና ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱን ማጠናቀቁን ነው የወረዳው አብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ያስታወቀው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply