የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የአድዋ ድልን በዓል በማስመልከት በባህር ዳር የፓናል ውይይት አካሂዷል       አሻራ ሚዲያ የካቲት 23/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር 125ኛውን የዓድዋ የድል በ…

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የአድዋ ድልን በዓል በማስመልከት በባህር ዳር የፓናል ውይይት አካሂዷል አሻራ ሚዲያ የካቲት 23/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር 125ኛውን የዓድዋ የድል በ…

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የአድዋ ድልን በዓል በማስመልከት በባህር ዳር የፓናል ውይይት አካሂዷል አሻራ ሚዲያ የካቲት 23/06/13/ዓ.ም ባህር ዳር 125ኛውን የዓድዋ የድል በዓል አስመልክቶ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አዲሱ ትውልድ ከዓድዋ ድል ምን ይማራል?” በሚል መሪ ሃሳብ በባሕር ዳር የፓናል ውይይት እያካሄደ አካሂዷል። በፓናል ውይይትም የተለያዩ ተሳታፊዎች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡ በክብር እንግድነት ከተገኙት መካከል ጀኔራል ተፈራ ማሞ ትውልዱ ታሪኩን ማወቅ፣ ታሪኩን መጠበቅ እና ታሪክ መሥራት ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ጨምረውም የአማራ ህዝብ አንድነቱን በማስጠበቅ መጓዝ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡… በውይይቱ መልዕክት ያስተላለፉት የባሕር ዳር እና አካባቢዋ የአብን አስተባባሪ ረዳት ኘሮፌሰር ስጦታው ቀሬ ኢትዮጵያ በታሪኳ የውጭ ወራሪዎችን ጣልቃ ገብነት እና የውስጥ ሳንካዎችን በተለያዩ ዘመናት ማስተናገዷን አውስተው ከነዚህ መካከል የዓድዋ ጦርነት አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል። የዓድዋ ጦርነት መነሻው ፋሽዝም የወለደው የሞግዚት አስተዳደር ከንቱ ቅዥት ነበር ያሉት ረዳት ፕሮፌሰር ስጦታው የነፃነታችን ዋስትና ደግሞ የአባቶቻችን ጀግንነት፣ አይበገሬነት እና ድል አድራጊነት ስነ ልቦና እና መንፈስ ነበር ብለዋል። የዚህ ዘመን ትውልድ የአባቶቹን የልዕልና ከፍታ ሊወርስ ይገባል ነው ያሉት። ለዓድዋ ጦርነት ድል መገኘት በርካታ ምክንያቶች ነበሩ ያሉት ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ የአፄ ምኒልክ የአመራር ጥበብ ግን መነሻ ነበር ብለዋል። ሕዝብ ታሪክ ይሠራል ያሉት ጀኔራል ተፈራ ታሪክ ለሚሠራው ሕዝብ በሳል፣ በሕዝብ ተቀባይነት ያለው እና ራዕይ ያለው መሪ ያስፈልገዋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡ ጀምሮ የሚያቋርጥ ሳይሆን የሚጨርስ ትውልድ ያስፈልጋል ያሉት ጀኔራል ተፈራ ትውልዱ የጀመረውን እንዲጨርስ “ታሪኩን ማወቅ፣ ታሪኩን መጠበቅ እና ታሪክ መሥራት ይኖርበታል በማለትም አክለዋል፡፡ የአድዋ ድል ያለ እምየ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ ከንቱ ነው ያሉት ደግሞ በመድረኩ ላይ የተገኘችው አርቲስት ወይንሽት አየነው ናቸው፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply