የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ማዕከላዊ ኮሚቴ 3ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ መጀመሩን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበ…

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ማዕከላዊ ኮሚቴ 3ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ መጀመሩን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት የሚያደርገውን ጉባዔ ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ እንደሚገኝ ፓርቲው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ማዕከላዊ ኮሚቴው የ2012 በጀት ዓመት እና የ2013 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የንቅናቄውን ሥራ አፈፃፀም እንዲሁም በቀጣይ የምርጫ ሥራዎች እና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply