የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ሴቶች በአማራ ፖለቲካ ውስጥ የማይተካ ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ምኅዳር ለመፍጠር የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥ…

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ሴቶች በአማራ ፖለቲካ ውስጥ የማይተካ ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ምኅዳር ለመፍጠር የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የፖለቲካ ጉዳዮች ዘርፍ ከአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ ሴት አመራሮቹ «የሴቶች ሚና በአማራ ፖለቲካ!» በሚል ርዕስ ትላንት ጥቅምት 8 ቀን 2013 ዓ.ም በዋና ጽ/ቤቱ ለ2ኛ ጊዜ ሥልጠና መስጠቱን አስታውቋል። የሥልጠናው ዓላማም የንቅናቄውን የሴት አመራሮች አቅም በማጎልበት በአማራ ፖለቲካ ውስጥ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል መሆኑን የገለፁት የአብን የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ አብን የሴቶችን የመሪነትና የውሳኔ ሰጭነት ሚና ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በውይይቱ የተካፈሉ ሴቶችም በአማራ ጠሉ ሥርዓት የመጀመሪያ ተጎጅዎች ሴቶች መሆናቸው ተገልጧል። በመሆኑም አብን የአማራን ሕዝብ የነፃነት፣ የፍትኅና የእኩልነት ጥያቄዎችን ለማስመለሥ በሚያደርገው ትግል ሴቶች የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡ አክለውም መሰል ሥልጠናዎች የሴቶችን አቅም በመገንባት ተሳትፏቸውን ለማሳደግ አይተኬ ሚና ስላለው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡ አብን የአማራ ሕዝብን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለማስመለስ እንዲሁም ለሁሉም ዜጎች የምትመች ጠንካራ አገር ለመፍጠር በሚያደርገው ትግል የሴቶች አስተዋፅኦ ከፍተኛና ትኩረት የሚሻ ነው ያሉት አቶ ክርስቲያን አብን በመላ አገሪቱ ለሚገኙ ሴት አመራሮቹና አባላት ቀጣይነት ያላቸው ሥልጠናዎችን መርኃግብር ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል የአብን የደሴ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በድርጅቱ ስትራቴጅዎች፣ ፖሊሲዎች እና በወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ ላይ በደሴ ከተማ ለአባላቱ ስልጠና ሰጥቷል። በተመሳሳይ የአብን የምዕራብ ጎንደር ዞን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከገንዳውኃ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመሆን ለንቅናቄው የቀበሌ ሥራ አስፈፃሚዎች በንቅናቄው መተዳደሪያ ደንብ፣ ዓላማና ፕሮግራም ዙሪያ ሥልጠና መስጠቱን አስታውቋል ሲል አብን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply