የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) አመራሮችና አባላት በሕግ ማስከበር ላይ ለሚገኘው የመከላክያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሽያ በደሴ ከተማ የደም ልገሳ አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) አመራሮችና አባላት በሕግ ማስከበር ላይ ለሚገኘው የመከላክያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሽያ በደሴ ከተማ የደም ልገሳ አደረጉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአብን ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ከሃዲውና አገር አፍራሹን የትሕነግ ስብስብ ድባቅ በመምታት የአገር ኅልውናን ለማረጋገጥና ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር ለሚፋለመው የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሽያና ፋኖ እንዲሁም ለአገር መከላከያ ሠራዊት በወልቃይትና በራያ ግንባሮች በአካል በመገኘት የመጀመሪያውን ዙር ድጋፍ አድርጓል። በራያ ግንባር ለተሰለፈው የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሽያና ፋኖ እንዲሁም ለአገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ያደረገው የአብን ልዑክ ዛሬ ኅዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም በደሴ ሪፈራል ሆስፒታል በመገኘት ለአገርና ለሕዝባቸው በከፈሉት መስዋዕትነት የቆሰሉ የሠራዊቱ አባላትን በመጎብኜት «ሕይወቱን ለሚሰጠኝ ደሜን እሰጣለሁ!» በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርኃ ግብር አከናውነዋል፡፡ የአገርን አንድነት ለመጠበቅና የሕዝባችንን ደኅንነት ለማስጠበቅ የሕይወት መስዋዕትነት ለሚከፍለው የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሽያና ፋኖ እንዲሁም የአገር መከላከያ ሠራዊት አብን ድጋፉን በተለያዬ መንገድ እያደረገ ነው ያሉት የአብን ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ የደም ልገሳ መርኃ ግብሩም የዚህ አካል ነው ብለዋል። ጽንፈኛው ቡድን ለሕግ እስኪቀርብ ድረስ አብን የሚያደርገውን ሁሉንአቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁት አቶ በለጠ፤ መላ ኢትዮጵያውያንም ሽብርተኛው የትሕነግ ቡድንን በመደምሰስ የአገርን ኅልውና ለማስጠበቅ በጀግንነት ለተሰለፈው የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ እስካሁን እያደረጉ ላሉት ሁሉንአቀፍ ድጋፍ አመስግነው በቀጣይም ድጋፉ እስከድል ድረስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። በሌላ በኩል የልዑካን ቡድኑ ከደም ልገሳው በኋላ ከደቡብ ወሎ ዞን የአብን የዞንና የወረዳ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ክልላዊ፣ አገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ ሰጥቷል። አብን በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply