የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ከመተከል ለተፈናቀሉና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም…

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ከመተከል ለተፈናቀሉና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም…

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ከመተከል ለተፈናቀሉና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአብን ብሔራዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቅርቡ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በትሕነግ ምትክ አይዞህ ባይ ያገኘው የቤኒሻንጉል ክልላዊ መዋቅር በአማራና አገው ሕዝባችን ላይ በመተከል ዞን ዘግናኝና አረመኔያዊ ድርጊቶች እንዲፈጸሙ አስቻይ መድረክ ሆኖ እያገለገለ መሆኑ ተገልጧል። በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ የዘር ማጥፋትና የማፈናቀል ወንጀል ለመቀልበስ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጥሪ ያቀረበው አብን ተጎጅዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማገዝም ድርጅቱ በሚኖረው ሚና ዙሪያ መክሮ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል። ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚው አብን በተለያዩ ጊዜያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እንዳደረጋቸው ድጋፎች ሁሉ ከመተከል ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ወስኖ የልዑካን አባላትንም ሰይሞ የነበረ ሲሆን ልዑኩም ትላንት ታኅሣሥ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ከድርጅቱ የሥራ ማስኬጃ ገንዘብ ወጭ በማድረግ በጥቃቱ ከመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ድጋፉን አድርጓል። አብን ባለፉት ሁለት ከመንፈቅ ዓመታት በአማራ ሕዝብ ላይ የተሰራውን ርዕዮታዊ፣ ሕጋዊና መዋቅራዊ የጥላቻና የጭቆና ሥርዓት ከናካቴው ለማስወገድና ሕዝባችን ኅልውናው ተከብሮ እንዲኖር ለማስቻል ቆራጥ ትግል እያደርገ መሆኑን የገለፁት የልዑኩ መሪ የአብን የቀድሞው የኢኮኖሚ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ካሱ ኃይሉ አብን ዛሬም የትሕነግን ውርስ ለማስቀጠል በሚመኙ ኃይሎች ሕዝባችን በገዛ ቀየው ተሳዳጅና ተገዳይ እንደይሆን ከሁሉም አማራዊ ኃይሎች ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አክለውም ዝቅተኛው የመንግሥት ኃላፊነት ሕግ በማስከበር የዜጎቹን ደኅንነት መጠበቅ ቢሆንም ይኼን ኃላፊነቱን በቤንሻንጉልና በኦሮሚያ ክልል በአግባቡ እየተወጣ ባለመሆኑ በሕዝባችን ላይ እየተፈፀመ ላለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ከተጠያቂነት አያመልጥም ብለዋል። ጥቃቱ በክልሉ ባሉ መንግስታዊ መዋቅሮች ጭምር የተደገፈ መሆኑን የገለፁት ተጎጅዎቹ ከአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ባለፈ በዘላቂነት የሚካሱበትንና የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ላይ ሁሉም አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ ድጋፉ አብን ካለው አነስተኛ የሥራ ማስኬጃ ገንዘብ ቀንሶ ከጎናችሁ መሆኑን ለማሳየት ያደረገው ነው ያሉት አቶ ካሱ በቀጣይም በአካባቢው የሕግ የበላይነትን በማስፈን ተጎጅዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገውን እንቅስቃሴ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ ተባብሮ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ ለተጎጅዎች መንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሁሉም ኢትዮጵያዊ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግ የጠየቁት አቶ ካሱ መንግስትና የኢትዮጵያ መጻዒ ዕድል ያሳስበናል የሚሉ አካላት በሙሉ በአማራ ሕዝብ ላይ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማስቆም ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ተናግረዋል። አብን በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳጋራው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply