የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰለፍ ጠራ፤ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 14/2013 ዓ….

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰለፍ ጠራ፤ /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 14/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ የአማራን ሕዝብ እየገጠሙት ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያየ እንደሆነም ገልፆአል። በውይይቱ በዋናነት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በአማራዎች ላይ እየደረሰ የሚገኘውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እና ሌሎች መዋቅራዊና ሕግ ሰራሽ መገለሎችን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በ «አማራ ክልል» በሚገኙ ከተሞች በመጭው ረቡዕ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሁም በአዲስ አበባ እሁድ ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲደረግ ወስኗል። ዝርዝር አፈፃፀሙን በቀጣይ የምንገልፅ ይሆናል ሲልም አስታውቋል። https://youtu.be/aJvcmASL_t0

Source: Link to the Post

Leave a Reply