የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የጎንደር ከተማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የአባላቱንና የአመራሮቹን አቅም ለመገንባት የተለያዬ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገለፀ። አሻራ ሚዲያ…

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የጎንደር ከተማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የአባላቱንና የአመራሮቹን አቅም ለመገንባት የተለያዬ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገለፀ። አሻራ ሚዲያ ህዳር 19/2013 ዓ•ም ባህርዳር የአብን የጎንደር ከተማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ የክ/ከተማና የቀበሌ ሥራ አስፈፃሚዎች፣ የመሰረታዊ ድርጅት አመራሮች፣ የምክር ቤት፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን አባላት ዛሬ ኅዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም በጎንደር ከተማ አዲሱ አዳራሽ በንቅናቄው የርዕዮተ-ዓለም፣ የትግል ስትራቲጂዎችና ግቦች እንዲሁም በወቅታዊ አገራዊ እና ቀጠናዊ የፖለቲካ ማዕቀፎችና አሰላለፎች ዙሪያስልጠና ሰጥቷል። የሥልጠናው ዓላማ የንቅናቄው አመራሮች ወቅታዊውን የኃይል አሰላለፍ ተረድተው ድርጅታዊ ተልዕኳቸውን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲያከናውኑ አቅም ለመገንባት መሆኑን የአብን የጎንደር ከተማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክብርት ገልፀዋል። ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ የአባላቱንና የአመራሮችን አቅም ለመገንንባት የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑንና በቀጣይም ሕዝባዊ ውይይቶችን ለማካሄድ አቅደው እየሰሩ መሆኑን አቶ አሸናፊ ተናግረዋል። አብን አገራዊ ማኅበረ-ፖለቲካው የተስተካከለና ፍትኃዊ እንዲሆን አማራነት የዝቅተኛ ግምት ሰለባ የሆነበት አጉል ባኅል ቀሪ መሆን አለበት ብሎ ያምናል። ይሄን ለማረጋገጥም ትግላችን ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናልም ተብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply