የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በመጪው ረቡዕ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ/ም ለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ድጋፉን የሚሰጥ መሆኑን ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር ደብረ ብርሀን ቅ/ጽ/ቤት አስታወቀ።…

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በመጪው ረቡዕ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ/ም ለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ድጋፉን የሚሰጥ መሆኑን ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር ደብረ ብርሀን ቅ/ጽ/ቤት አስታወቀ።…

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በመጪው ረቡዕ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ/ም ለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ድጋፉን የሚሰጥ መሆኑን ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር ደብረ ብርሀን ቅ/ጽ/ቤት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አብን በመጪው ረቡዕ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በአማራነታቸው ብቻ እየተመረጡ በጅምላ ለተገደሉ ወገኖቻችን ፍትህ የምንጠይቅበት እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ የምናሳውቅበት ይሆናል ማለቱን ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር ደብረ ብርሀን ቅ/ጽ/ቤት አውስቷል። ምንም እንኳ አብን ሰልፉን በበላይነት ሀላፊነት ወስዶ ይምራው እንጂ የሁሉም አማራ ነው፤ ሁሉም አማራ የቱም አይነት ልዩነት ሳይገድበው ሊሳተፍበት የሚገባ ነው ሲል እንደሚጋራው አስታውቋል። ሰልፉ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የሚመለከታቸው የመንግስት ሀላፊዎች ጨምሮ ሁሉም ሰው ሀላፊነት በተሞላበት መንገድ ተቃውሞውን በሰለጠነ መንገድ መግለፅ ይኖርበታል ነው ያለው። የመንግስት አካላት ክልከላ ላይ ከማተኮር ይልቅ ለሰልፉ በቂ ጥበቃ ለመስጠት ዝግጅት ከወዲሁ ማድረግ ቢችሉ መልካም እንደሚሆን የገለፀው ማህበሩ አብን ረቡዕ ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ ተገቢውን እገዛ እንደምናደርግ በድጋሜ እንገልፃለን ሲል አረጋግጧል። በመጨረሻም “ሞታችንን ለመግለፅ የማንንም ፍቃድ አንሻም።” ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply