የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡የፓርቲዉ ሙሉ መግለጫ የሚከተለዉ ነው፡-የኢትዮጵያ መንግስት ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ትሕነግ) እያለ…

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የፓርቲዉ ሙሉ መግለጫ የሚከተለዉ ነው፡-

የኢትዮጵያ መንግስት ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ትሕነግ) እያለ ከሚጠራው አሸባሪ ቡድን ጋር ሲያደርግ የነበረውን የሰላም ንግግር በተመለከተ ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሂደቱን በንቃት እየተከታተለ እና አቋሙን በየጊዜው እያሳወቀ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በኢትዮጵያ መንግስት እና በአሸባሪው ትሕነግ መካከል ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረገው የሰላም ሥምምነት ውል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተረጋገጠው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ያጋሩትን የሥምምነት ሰነድ ፓርቲያችን አብን ለመመልከት ችሏል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ይህን ባለ አስራ አምስት አንቀጽ ሆኖ የተዘጋጀውን የሰላም ሥምምነት ውል በጥንቃቄ እና ጊዜ ወስዶ የመረመረ ሲሆን ፣ ፓርቲያችን አቋም ለያዘባቸው ጉዳዮች በከፊል ምላሽ የሰጠ እና ሥምምነቱ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ያሉት መሆኑን ለመረዳት ችሏል፡፡

ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር እያለ የሚጠራው ቡድን ከአምስት አስርት ዓመታት ጠመንጃ አንጋችነት ታሪክ በኋላ፣ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ትጥቅ ለመፍታት መፈረሙ እና በ30 ቀናት ውስጥ ትጥቁን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለማስረከብ ሥምምነት ላይ መደረሱ በሥምምነቱ መሰረት ከተፈጸመ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ትልቅ የታሪክ እጥፋት መሆኑን እና በሀገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ትልቅ ድርሻ እንደሚያበረክት እና በሽብር ቡድኑ እገታ ውስጥ ለቆየው እና ላለው የትግራይ ሕዝብም እፎይታ የሚሰጥ እንደሚሆን ፓርቲያችን አብን ያምናል፡፡

ሥምምነቱ በአፍሪካ ሕብረት ስር “ለአፍሪካ ፈተናዎች አፍሪካዊ መፍትሄዎች” በሚል መርህ ፣ በአፉሪካ ለአፍሪካውያን የተሰራ መሆኑ እና በአፍሪካውያን ክትትል ስር ብቻ ተግባራዊ እንዲደረግ ሥምምነት የተደረሰበት አግባብ አጋጣሚውን ተጠቅመው ሀገራችን ኢትዮጵያን በማያቋርጥ ግጭት ውስጥ ለመዝፈቅ እና የቀውስ ማዕከል ለማድረግ የተሰለፉ ጠላቶቻችንን መመከት ያስቻለ እና መላው አፍሪካ ከወቅቱ የቅኝ አገዛዝ ስርዓት (Neocolonialism)ነጻ ለመውጣት ለሚያደርገው ተጋድሎ የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀ ክስተት መሆኑን ፓርቲያችን ያምናል፡፡

ታጣቂ ቡድኑ የአፍሪካ የሕግ ማዕቀፎችን እና የኢትዮጵያ ተቋማትን ሙሉ በሙሉ እውቅና ለመስጠት ሥምምነት ላይ መድረሱ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ ሀገራዊ ፈተና ሆኖ የዘለቀውን የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት ለመመከት የሚያስችል በመሆኑ ፓርቲያችን አብን እውቅና የሚሰጠው ታላቅ ሀገራዊ ድል ነው፡፡

በሰላም ሥምምነቱ ላይ ጦርነቱ የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ሕዳር 3 ቀን 2020 ዓ.ም) ስለመሆኑ እውቅና ማግኝቱ ፤ የሽብር ቡድኑ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ መሰል የሽብር ቡድኖች ስምሪት ላለመስጠት ፣ ላለማገዝ እና ላለመተባበር ግዴታ የገባበት መሆኑ ፤ ሥምምነቱ በኢትዮጵያ መንግስት እና በሕግ አግባብ በሽብርተኝነት በተፈረጀ አንድ ታጣቂ ቡድን መካከል የተደገረ ስለመሆኑ የተረጋገጠበት መሆኑ ፤ የሽብር ቡድኑ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱ እና የሰላም ንግግር መድረኩን ወደ ብሔራዊ የምክክር መድረክ ለመቀየር የተደረገው ጥረት የከሸፈበት መሆኑ ከሚጠቀሱ የሥምምነቱ ጠንካራ ጎኖች ውስጥ ናቸው፡፡

ይሁንና የሰላም ሥምምነቱ እጥረቶች ያሉበት ስለመሆኑም ፓርቲያችን ለማስተዋል ችሏል፡፡

ፓርቲያችን አብን የሀገር አንድነትን ለማጽናት እና ለዘላቂ ሰላም ሲባል በብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዕቀፍ ውስጥ ሊፈጸሙ የሚችሉ አንዳንድ እርምጃዎች ላይ ተቃውሞ የማይኖረው ቢሆንም፣ ከምስረታ ሰነዱ ጀምሮ አማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ ኁልቆ መሳፍርት የሌለው መከራ በሕዝባችን ላይ ያደረሰን ፣ ፋሽስታዊ የፖለቲካ ፕሮግራምን እና ሽብርን የፖለቲካ ግብ ማስፈጸሚያ አድርጎ የቀረጸን “ነጻ አውጭ” ድርጅት የፖለቲካ ኅልውና ለማስቀጠል የተደረሰው ሥምምነት ፣ ሥምምነቱ የታለመለትን “የሀገራችን ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ፣ የግዛት አንድነት እና ሀገራዊ አንድነት የማክበር” መርህ የሚጣረስ እና ለሀገራችን ሰላም እና አንድነት ቀጣይ ስጋት እና አደጋን የሚጋርጥ በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ስህተት ነው፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክም ሆነ በሌሎች ሀገሮች የፖለቲካ ታሪክ እንደሚታወቀው “ነጻ አውጭ ግንባሮች” ሽብርን እንደ ሁነኛ የፖለቲካ ትግል መሳሪያ አድርገው የሚጠቀሙ በመሆናቸው ፣ ለሀገር ሉዓላዊነት ፣ የግዛት አንድነት እና ሀገራዊ አንድነት ቁሚያለሁ በሚል ማንም ሀገር እና መንግስት ሕጋዊ እውቅና የማይሰጣቸው እና በሕገወጥነት ተፈርጀው ኅልውናቸውን ለማክሰም እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያም አሁን ትጥቅ ለመፍታት የተስማማውን ትሕነግ ጨምሮ ሌሎች “ነጻ አውጭ ግንባሮች” በሀገራችን የፖለቲካ ምኅዳር ላይ ከተከሰቱበት ያለፉት አምስት ዓስርት አመታት ወዲህ በሀገር ሉዐላዊነት ፣ የግዛት አንድነት እና ሀገራዊ አንድነት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሳቸው የሩቅ እና የቅርብ ትዝታችን ብቻ ሳይሆን ፣ አሁንም እየኖርንበት ያለ ሃቅ ነው፡፡

ሌላው የሥምምነቱ እጥረት ሆኖ ሊቆጠር የሚችለው የሽብር ቡድኑ የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሳባቸው የአማራ ሕዝብ ክፋይ የሆኑት እና አማራዊ ማንነታቸውን ለማስጠበቅ ብርቱ ትግል በማድረጋቸው ለዘር-ማጥፋት ድርጊት ተጋልጠው የቆዩትን የወልቃይት እና የራያ አካባቢዎች በሚመለከት የሰፈረው የስምምነት ቃል ነው፡፡

አካባቢዎቹ በስምምነቱ የመሸጋገሪያ ተግባራት ድንጋጌ (Transitional Measures) አንቀጽ 10(4) ስር ራሳቸውን ችለው የሚታዩ ስለመሆኑ የሥምምነት ቃል መስፈሩ ለጊዜው እፎይታ የሚሰጥ ፣ በትግራይ (Tigray Proper) ከሚቋቋመው አስተዳደር በተለየ ሁኔታ የሚስተናገድ ስለመሆኑ የሚያመላክት እና ፓርቲያችን አብን በዚሁ አግባብ ግንዛቤ የያዘበት ቢሆንም ፣ አካባቢዎቹ በአማራ ክልል ስር እንደሚቀጥሉ በግልጽ በስምምነቱ ላይ አለመስፈሩ የስምምነቱን ክሽፈት እንዳያስከትል ስጋት ላይ የሚጥል ነው፡፡

የአማራ ሕዝብም ሆነ የጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ሳያገኝ ከትሕነግ የፖለቲካ ፕሮግራም ገጽ በገጽ ተገልብጦ በሥራ ላይ በዋለ ሕገ-መንግስት እና ሕገ-መንግስቱ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት በኃይል ወደ ትግራይ የተካለሉትን የወልቃይት እና የራያ አካባቢዎችን በሕገ-መንግስቱ አግባብ ውሳኔ ያገኛሉ በሚል በዚሁ የሥምምነቱ ክፍል ሥምምነት የተደረሰበት አግባብ ለሶስት አስርት ዓመታት በከፍተኛ ግፍ እና እንግልት ሥር ለኖረው የአካባቢው ማኅበረሰብ እና ሕዝባችን ከወዲሁ ዋስትና የማይሰጥ በመሆኑ ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን አሳስቦታል፡፡

የወልቃይት እና የራያ ጉዳይ ውድ ዋጋ የተከፈለበት የማንነት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ፣ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና ያለው እና የሀገራችን ኢትዮጵያ የብሔራዊ ደኅንነት የሚረጋገጥበት ጉዳይ መሆኑን ግንዛቤ እንዲያዝበት ፓርቲያችን ያሳስባል፡፡

ስለሆነም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል:-
፩. በሰላም ሥምምነቱ በተቀመጠው አግባብ የሽብር ቡድኑ ትጥቁን እንዲፈታ መንግስት በሙሉ አቅሙ እና ትኩረት እንዲሰራ፤

Source: Link to the Post

Leave a Reply