You are currently viewing የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የማዕከላዊ ኮሚቴና የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባውን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ***** የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ማዕከላዊ ኮሚቴ መጋቢት 9 እና 10 ቀን…

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የማዕከላዊ ኮሚቴና የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባውን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ***** የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ማዕከላዊ ኮሚቴ መጋቢት 9 እና 10 ቀን…

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የማዕከላዊ ኮሚቴና የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባውን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ***** የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ማዕከላዊ ኮሚቴ መጋቢት 9 እና 10 ቀን በባህር ዳር ባደረገው ስብሰባ፦ 1. የትግራይ ወራሪ ኃይል የከፈተብንን ጦርነት ለመከላከል ያደረግነውን የህልውና ዘመቻ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። የህልውና ዘመቻው የተመራበትን ሂደት ደካማና ጠንካራ ጎኖች በመለየት፤ ወራሪው ኃይል አከርካሪው ተሰብሮ ቢሸሽም አሁንም ከአማራና ከአፋር ክልል ጨርሶ ባለመውጣቱ ለሀገርና ለህዝብ ስጋት ሆኖ መቀጠሉን አስቀምጧል። አብን በዘመቻው ላይ በግንባርም በደጀንም ያደረገውን ታሪካዊ ፍልሚያ በጥልቀት በመመርመር፣ አሁንም የአማራ ህዝብ ወራሪው ከናካቴው እስኪደመሰስ በተጠንቀቅ እንዲቆም ሁለገብ ዝግጅት እንዲያደርግና ንቅናቄያችንም የተጠናከረ ሚና እንዲጫወት አቅጣጫ አስቀምጧል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወረራው ያደረሰውን ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳት በመገምገም፣ ለተፈናቀሉ ሚሊዮኖች ወገኖቻችን የመልሶ ማቋቋምና የዘለቄታውም የክልሉ መልሶ ግንባታ ላይ ሊኖረው የሚገባውን ድርሻ ለይቷል። 2. ማዕከላዊ ኮሚቴው በድርጅቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ተዘጋጅቶ በቀረበለት በንቅናቄው የ5 ዓመት ስትራቴጂክ አቅድ ላይ በጥልቀት በመወያየትና የማሻሻያ ሀሳቦችን በማካተት አፅድቋል። 3. በተጨማሪም የንቅናቄው ማ/ኮሚቴ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይም በጥልቀት ተወያይቷል። በዚህም መሠረት በሀገሪቱ እየተባባሰ የመጣው የደህንነት ስጋት አሳሳቢ መሆኑን በመገምገም አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚያሻውና መንግሥት በዚህ ረገድ ተቀዳሚ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቋል። በተጨማሪም በ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ እየተነሳ ያለው ጥያቄ ከተማሪዎችና ወላጆች አልፎ የማህበረሰባችን ጥያቄ በመሆኑ አገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅትና ትምህርት ሚኒስቴር አስቸኳይ እልባት እንዲሰጡት እያሳሰብደን፣ እስከዚያው ድረስ ግን የተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምደባ እንዲዘገይ በአጽንኦት እንጠይቃለን። 4. ማ/ኮሚቴው በንቅናቄው የመዋቅራዊና የአሰራር ቁመና በመፈተሽ፣ ንቅናቄው የቆመለትን ሀገራዊና ህዝባዊ ተልዕኮ በላቀ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችል የአመራር ስምሪት ማስተካከያ አድርጓል። በዚህም መሠረት፦ 1) አቶ ዩሱፍ ኢብራሒም – ም/ሊቀመንበርነታቸውን 2) አቶ አዲሱ ሐረገወይን – የፖሊሲና ስትራቴጂ ኃላፊነታቸውን 3) አቶ መልካሙ ጸጋየ – የማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበው ማዕከላዊ ኮሚቴው መርምሮ ተቀብሎ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴውን እንደገና አደራጅቶታል። አዲሱ አስፈፃሚም፦ 1) ዶ/ር በለጠ ሞላ – ሊቀመንበር 2) አቶ መልካሙ ሹምዬ – ም/ሊቀመንበር 3) ዶ/ር ቴዎድሮሥ ኃይለማርያም – የማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ 4) ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ – የውጭ ጉዳዮችና ዓለማቀፍ ግንኙነት ኃላፊ 5) አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም – የህግና ስነ–ምግባር ጉዳዮች ኃላፊ 6) አቶ ጣሂር መሃመድ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ 7) አቶ ጋሻው መርሻ – የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ 8 አቶ ክርስቲያን ታደለ – የፖሊሲና ስትራቴጂ ኃላፊ 9) አቶ ሀሳቡ ተስፋው – የአደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ ወስኗል። በተጨማሪም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የድርጅቱን 3ኛ ጠቅላላ ጉባኤ መጋቢት 11 ቀን በማካሄድ በተሳካ ሁኔታ አጠናቅቋል። በዚህም መሠረት፦ 1. የማዕከላዊ ኮማቴ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት በማድረግ አፅድቋል። 2. ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በሰጠው አቅጣጫ መሠረት በንቅናቄው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ማሻሻያዎችን በማድረግ አፅድቋል። 3. የድርጅታዊ ሪፎርም ላይ ጠቅላላ ጉባኤው በጥልቀት በመወያየት፣ የማ/ኮሚቴውን እንደገና ለማደራጀት የአመቻች ኮሚቴ በማቋቋም በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ አጠቃላይ ሪፎርም እንዲያደርግ ተስማምቷል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለሀገራቸውና ለህዝባቸው መስዋዕትነት የከፈሉ ሰማዕታትን በመዘከር ፣ መላው የድርጅቱ አመራርና አባላት የተሰለፉበትን ታላቅ ተልዕኮ ለማሳካት በአዲስ መንፈስ እንዲሰለፉ ጥሪ ያቀርባል። ለንቅናቄዉ ጉባኤ መሣካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ የአማራ ክልል መንግሥትና የፀጥታ ኃይል፣ እንደዚሁም የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን አካላት የከበረ ምሥጋና ያቀርባል። አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ ! ባህር ዳር ፣ ኢትዮጵያ መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply