የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የባህር ዳር ከተማና አካባቢው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በአውስትራሊያ- ኒው ሳውዝ ዌልስ የአማራ ማህበር ጋር በመተባበር በአማራ ህዝብ ላይ ጠላት ባደረገው ኢሰ…

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የባህር ዳር ከተማና አካባቢው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በአውስትራሊያ- ኒው ሳውዝ ዌልስ የአማራ ማህበር ጋር በመተባበር በአማራ ህዝብ ላይ ጠላት ባደረገው ኢሰብአዊ ወረራ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሰብዓዊ እርዳታ በማድረግ ላይ ይገኛል። ጽ/ቤቱ በውጭ ከሚኖሩ ወገኖቻችን የተለገሰውን ገንዘብ የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ አንገብጋቢ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውንና የእርዳታ አይነት በመለየት እያሰራጨ ይገኛል። ደቡብ ጎንደር እብናት ከተማ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተጎጂዎች በገንዘብ ከ300,000 ሺህ ብር በላይ የሆነ ብርድልብስ፣ የመኝታ ስጋጃ፣ የማብሰያ ቁሳቁስና የምግብ መስሪያ ግብዓት በመያዝ በቦታው በመገኘት ለተጎጂዎች በቀጥታ በማሰራጨት ላይ ነው። በቀጣይም ወረራውን በመመከት በቀጥታ በጦርነት ላይ ባሉበት ወቅት የጦር ጉዳት ለደረሰባቸውና ህክምና ላይ ለሚገኙ የአማራ ፋኖ፣ የአማራ ልዩ ሀይልና ሚኒሻ አካላት ድጋፉን እንደሚቀጥል አስተባባሪ ኮሚቴው አሳውቋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply