የአማራ ተማሪዎችን ሁሉም ባለበት ቦታ እና ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ መደገፍ እንዳለበት ማህበሩ አሳሰበ !! /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// የአማራ ተማሪዎችን ሁሉም…

የአማራ ተማሪዎችን ሁሉም ባለበት ቦታ እና ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ መደገፍ እንዳለበት ማህበሩ አሳሰበ !! /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// የአማራ ተማሪዎችን ሁሉም ባለበት ቦታ እና ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ መደገፍ እንዳለበት ማህበሩ አሳሰበ… የአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ ለአንድ ተማሪ አንድ ደርዘን ደብተርና አንድ ደርዘን እስኪርቢቶ በሚል መርሀ ግብር በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች በማሰባሰብ ላይ ይገኛል፡፡ በቁሳቁስ ማሰባሰብ ምረ ግብሩ ከመንግስት መስሪያ ቤቶች ፤ ከንግድ ማህበረሰብ ዓባላትንና ከመልካም ፈቃደኛ በጎ አድራጊዎች ሁሉ እያሰባሰበ ይገኛል፡፡ የአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ በዚህ መርሀ ግብሩ በዛሬው ዕለት ከአማራ ውሀ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት አውስኮድ የተደረገውን ድጋፍ ተረክቧል፡፡ በዕለቱ የአማራ ውሀ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት አውስኮድ የገብያ ጥናት ባለሙያ እንዳሉት አውስኮድ የክልሉ የመንግስት የልማት ድርጅት እንደመሆኑ መጠን በርካታ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የአማራ ተማሪዎች ማህበር የአባላት ጉዳዮች አስተባባሪ ሀብተማሪያም ሞላ ሁሉም የሚችለውን በማድረግ ለትምህርትና አቅም ለሌላቸው አቅም ለመሆን መተባበር እንደሚያስፈልግ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ ከነሀሴ 15 /2012 ዓ.ም እስከ አሁን ድረስ አንድ መጽሀፍ ፤ደርዘን ደብተርና እስክርቢቶ ለአንድ ተማሪ በሚል መርሀ ግብሩ ላይ ለተሳተፉ እና አስተዋዕጾኦ ላበረከቱ ባለሀብቶች፤የግልና የመንግስት ተቋማት፤የመንግስት የልማት ድርጅቶች፤የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች፤ እሁድ ጥቅምት 15 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር ከተማ በኦሊቭ ሆቴል የእውቅና አሰጣጥ ስነስርዓት እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ ዘጋቡ ማርሸት ፅሐው

Source: Link to the Post

Leave a Reply