የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ሊቀ መንበር እሸቱ ጌትነት በባህር ዳር መታፈኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 7 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማ…

የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ሊቀ መንበር እሸቱ ጌትነት በባህር ዳር መታፈኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 7 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ሊቀ መንበር እሸቱ ጌትነት ታህሳስ 07/2015 ዓ.ም እኩለ ቀን አካባቢ በሰዓቱ አብሮት ከነበረ መታገስ ጸጋ ከተባለ ወጣት ጋር ታፍኖ ተወስዷል። አፈናው የተፈጸመው በባሕር ዳር ከተማ ዋናው የገበያ ማዕከል አካባቢ “የክልሉን” የአድማ ብተና ፖሊስ የደንብ ልብስ በለበሱ አካላት መሆኑን አተማ አስታውቋል። አተማ እስከአሁን ድረስ የት እንደሚገኙ አድራሻቸውን ለማወቅ አልተቻለም ብሏል። ከክልሉ ውጭ በአማራ ተማሪዎች ላይ ከሚፈጸመው ተደጋጋሚ እገታ በተጨማሪ የማህበሩን ሥራ አስፈጻሚዎች ማሰርሩ እና ማዋከቡ ተባብሶ ቀጥሏል ነው የተባለው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply