
#የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ስራ አስፈፃሚዎች አርበኛ ዘመነ ካሴ ወህኒ ቤት በመሄድ ጠየቁ! መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) አባላት እና ስራ አስፈፃሚዎች ዛሬ ማለትም 04/07/2015 ዓ.ም ሰባትአሚት ማረሚያ ቤት በመሄድ አርበኛ ዘመነ ካሴን ጠይቀውታል። ” ትግል ዘመን በፈጠረልን የማህበራዊ ትስስር ገፅ ከምንወጣው ንዴት ይልቅ የታመቀ ቁጭት ሊኖረው ይገባል። እንደ ኒውዩክሌር መብላላትም አለበት ከዛ ነው ጥሩ የሚተኮስ ነገር የሚወጣው” አርበኛ ዘመነ ካሴ ለአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) አባላት እና ስራ አስፈፃሚዎችን ከመከራቸው ምክር መካከል ይገኝበታል ። በተመሣሣይ በነገው ዕለት የአርበኛውን የልደት ቀን በማስመልከት የባህርዳር እና አካባቢው ወጣቶች እንደሚጠይቁት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። #መልካም ልደት “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post