የአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ በአማራ ተማሪዎች ጉዳይ ላነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ እያገኘ አለመሆኑን ጠቅሶ በቅርቡ ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን እንደሚጀምር አስታወቀ። አማራ ሚዲያ…

የአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ በአማራ ተማሪዎች ጉዳይ ላነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ እያገኘ አለመሆኑን ጠቅሶ በቅርቡ ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን እንደሚጀምር አስታወቀ። አማራ ሚዲያ…

የአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ በአማራ ተማሪዎች ጉዳይ ላነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ እያገኘ አለመሆኑን ጠቅሶ በቅርቡ ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን እንደሚጀምር አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ባለፉት ሶስት ዓመታት ማህበራችን ህጋዊ ፈቃድ አግኝቶ መንቀሳቀስ ከጀመረበት ወቅት ጀምሮ በመላ ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ፣በትግራይ በደቡብ ክልሎች እንደ ህዝብ በአማራ ላይ በተማሪ ደረጃም በልዩነት የአማራ ተማሪዎች ሲፈናቀሉ፣ሲገደሉ እንደነበር በተከታታይ ስናጠና የጥናት ውጤቱንም ይፋ ስናደርግ እና ከመንግስት ጋር ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ ስንታገል ቆይተናል ብሏል የአተማ ስራ አስፈጻሚ ዛሬ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ። ሀገሪቱ ያለችበትን ተቀያያሪ የፖለቲካ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የተከሰቱ ችግሮችን መንግስት በመዋቅሩ እንዲፈታ የመነሻ ሀሳብ እና የመፍትሔ አቅጣጫ ከመስጠት ጀምሮ እያንዳንዱን አካሄዳችን በህግ ገድቦ ስለመቆየቱ ነው ያወሳው። በአንድ በኩል ብሔራዊ ትስስሩ ላይ ጫና ላለመፍጠር በሌላ በኩል ከለውጥ ማግስት ለተሰየመው መንግስት የመርጊያ ጊዜ ለመስጠት ከልክ በላይ በድርድርና በውይይት ችግሮች እንዲፈቱ አስቸጋሪ ወቅቶችን በትዕግስት ለማለፍ ስለመሞከሩም ጠቅሷል። ባሳለፍናቸው ሶስት ዓመታት አማራ እየተባሉ ተማሪዎቻችን ሲገደሉ ሬሳ ተቀብለን የቀረውን ትውልድ ለማሻገር በሚል አንገት ደፍተን ለማሳለፍ ሞክረናልም ብሏል። ነገር ግን እንደ ህዝብ ከአምናው የቀጠለ የዘር ፍጅት አሁንም በተከታታይ እየተካሄደ ስለሆነ መንግስትም ችግሩን በትክክል የመፍታት አቅም ይፈጥር እንደሆነ በሚል የተሰጠውን ጊዜ መጠቀም ባለመቻሉ፣ይልቁንም አጉል እምነት ዕለት ዕለት ለችግር እያጋለጠን እንዳለ ተገንዝበናል ሲል አስታውቋል። በመሆኑም የ2013 የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አሁንም በህዝቡ ዘንድ እየደረሰ እንዳለው እልቂት ፣ተቋማቱ የተማሪ ደህንነትን በሚመለከት ምንም አስተማማኝ ሁኔታ እንዳልፈጠሩ እና አሁንም የተማሪዎቻችን መገደያ ሆነው እንደሚቀጥሉ ገምግመናል ብሏል አተማ በአስቸኳይ መግለጫው። ስለሆነም በመጭው የትምህርት ዘመን ማንኛውም የአማራ ተማሪ በትግራይ፣በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ዩኒቨርሲቲዎች እንዳይሄድ ስንል ምክረ ሀሳብ አቅርበናል ነው ያለው። አተማ ሲቀጥል በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተጠቀሱት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የአማራ ተማሪዎች ትምህርት እስኪጀምሩ ድረስ ምንም ዓይነት የትምህርት እንቅስቃሴ እንዳይጀምሩ የሰላማዊ ተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ከወዲሁ እንደምንጀምር እንድታውቁ ሲል ነው ያሳሰበው። የማህበሩ ቅርንጫፎች ተማሪውን በማስተባበር ረገድ ራሳቸውን ዝግጁ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ አስተላልፈናል ያለው ማህበሩ የተማሪ ወላጆች ፣የክልሉ መንግስትና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም አጋር የሲቪክ ማህበራት ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪ እናስተላልፋለን ነው ያለው። በዓለም ላይ እርኩስ ተብሎ እንደተወገዘው የሆሎከስት የአይሁድ የዘር ፍጅት፣አማሮችን በአንድ ቦታ ሰብስቦ መረሸናቸው ልባችን ያደማ ክስተት በመሆኑ ሀዘናችን እንገልጻለን ብሏል። ይህን ለመመከት የሚያስችሉ አካሄዶችን ከመንደፍ ጀምሮ በተግባር እስከመሰለፍ በሚደርሱ የራስ መከላከል አርምጃዎች ለመሰለፍ ዝግጁ መሆናችን ለማሳወቅ እንወዳለን ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply