የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) በድሬድዋ ዩኒቨርስቲ የመብት ጥያቄ ባነሱ ተማሪዎች ላይ የሚፈጸመው እስር እና ወከባ እንዲቆም ጠይቋል፤ እስካሁን 13 ተማሪዎች ታስረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) በድሬድዋ ዩኒቨርስቲ የመብት ጥያቄ ባነሱ ተማሪዎች ላይ የሚፈጸመው እስር እና ወከባ እንዲቆም ጠይቋል፤ እስካሁን 13 ተማሪዎች ታስረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በድሬድዋ ዩኒቨርሲቲ በአማራ ተማሪዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ወከባ፣እስር እና ከትምህርት ማገድ አስመልክቶ ከአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ) የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ:_ በድሬድዋ ዩኒቨርሲቲ በሚማሩ የአማራ ተማሪዎች ላይ ባለፉት ወራት በተለይም ደግሞ ከሐምሌ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በተለየ ሁኔታ ወከባና እስር እየተፈጸመባቸው ይገኛል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት አዲስ ተማሪዎች ከተቀበለበት ሰዓት ጀምሮ መረጋጋት የማይታይበት ሲሆን በተለያየ ጊዜ በተማሪዎች ላይ ለደረሱ ጥቃቶች ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ተማሪዎች ላይ ጭምር እርምጃ ሲወስድ ቆይቷል፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በሚማሩ የአማራ ተማሪዎች ላይ የማጥቃት ሙከራ የተደረገ ሲሆን ከድርጊቱ በተቃራኒ በቁጥር አሥራ ሦስት(13) የሚሆኑ የአማራ ተማሪዎች ተለይተው እንዲታሰሩ ተደርጓል፡፡ ምግብም እየቀረበላቸው እንዳልሆነ ሊጠይቋቸው የሄዱ ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡ በተያያዘም ሐምሌ 19 ቀን 2104 ዓ.ም አመለወርቅ አወቀ የተሰኘች የአማራ ተወላጅ ተማሪ ሕይወቷ ያለፈ ሲሆን ‹‹ሕይወቷ ያለፈው ተመርዛ ነው›› መባሉን ተከትሎ ዩኒቨርሲቲው ጉዳዩን እንዲያጣራ የጠየቁ ተማሪዎች ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ተማሪ አመለወርቅ በወቅቱ ወደ ክሊኒክ ደርሳ የነበረ ቢሆንም የሕክምና ባለሙያዎቹ መታወቂያ ካላመጣችሁ ሕክምና አንሰጥም በማለታቸው ምንም ሕክምና ሳታገኝ ሕይወቷ አልፏል፡፡ ምንም ጥፋት የሌለባቸው ተማሪዎች እንዲታሰሩ ከመደረጉም በላይ ሦስት(3) ተማሪዎች በቋሚነት፤አሥራ አንድ(11) የሚሆኑት ደግሞ ለሁለት ዓመታት በድምሩ አሥራ አራት (14) የአማራ ተማሪዎች ከትምህርታቸው እንዲታገዱ ዩኒቨርሲቲው ያልተገባ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ የታሰሩ ተማሪዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው:_ 1.ዮናታን ዘላለም 2. ዘሩባቤል እንየው 3. ዘመኑ የኔዓለም 4. ሙሉሰው በላይ 5. ተመስገን ፈንታሁን 6. ገነቱ አላዩ 7. አባይነህ ባዩ 8. ይገርማል ተዋበ 9. መሠረት ስጦታው 10. አቡኑ አዳነ 11. ዮሴፍ ዋስይሁን 12. ጤናው ምስጋናው 13. ቴዎድሮስ አዳነ ተማሪዎቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱና ወደ ትምህርታቸውም እንዲመለሱ አጥብቀን እንጠይቃለን! በመጨረሻም በተማሪ አመለወርቅ ሕልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቿ እና ለመዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን እንመኛለን!!! አተማ፡ የአማራ ትውልድ ተቋም!!! ነሐሴ 2 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply