የአማራ ተማሪዎች ማህበር የአድዋን ድል አከበረ  የአማራ ሚዲያ ማእከል የካቲት 24 2013 አ/ም ሸዋ አዲስ አበባ አተማ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፏል ለአማራ ተማሪወች ማህበር  አመራር…

የአማራ ተማሪዎች ማህበር የአድዋን ድል አከበረ የአማራ ሚዲያ ማእከል የካቲት 24 2013 አ/ም ሸዋ አዲስ አበባ አተማ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፏል ለአማራ ተማሪወች ማህበር አመራር…

የአማራ ተማሪዎች ማህበር የአድዋን ድል አከበረ የአማራ ሚዲያ ማእከል የካቲት 24 2013 አ/ም ሸዋ አዲስ አበባ አተማ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፏል ለአማራ ተማሪወች ማህበር አመራር እና አባላት፣ ለመላው የአማራ እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሁም ለጥቁር ህዝቦች በሙሉ እንኳን ለ125ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ! ኢትዮጵያ በእምየ ሚኒሊክ መሪነት የእቴጌ ጣይቱ ጥበብ እና የሌሎች አርበኞች አይበገሬነት ተጨምሮበት ጥቁር ህዝብ በጥቁር መሪ እየተመሩ የወቅቷ ኃያል ሀገር ጣልያንን ማሸነፍ መቻል በነጮች ፈላጭ ቆራጭነት ስር ለነበረችው የአፍሪካ ምድር ከተባበሩ እና እንደ ኢትዮጵያውያን በአንድነት በጠላቶቻቸው ላይ ከተነሱ ከአውሮፓዊያን ቀኝ ገዥወች ነፃ መውጣት እንደሚችሉ መንገድ ያሳየ ብቻ ሳይሆን ሰርቶ ያስመሰከረ፤ ሆኖ የኖረ ፤ ተፈትኖ ያለፈ ለጥቁር አፍሪካዊያን የጦርነት ንድፈ ሀሳብን አሥተምሮ አስገራሚ ጀብዱ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር እና በአይበገሬ አርበኞቻችን ብስለትና በሀገር ፍቅር መስዋዕትነት ከፍታ ተፈፀመ። ። የኢትዮጵያ ጦር በአምባላጌ፣በመቀሌ እና በአድዋ ባደረገው ጦርነት የበላይነትን መቀዳጀት ለአፍሪካውያን ተስፋ እና ኩራት ሲሰጥ ለአውሮፓውያን ድንጋጤን ፈጠረ። የነጭን ልዕለ ሃያልነት ጥያቄ ውስጥ ከተተ። ለእውነት የቆሙ ጣሊያናውያንም ” ቪቫ ሚኒሊክ”! ”ቪቫ ጣይቱ” ሲሉ አወደሡ። አሜሪካኖች ለሰፋፊ እርሻቸው የሚያገለግሉ ባሮችን ለ500 አመታት ያህል እንደ እቃ ያጓጉዙ የነበረውን የዘመናት ጭቆና እና የስነ ልቦና ቁስል ህክምና ያደረከው የጥቁሮች ነፃነት እና የኢትዮጵያ ድል በአድዋ ተራራ ላይ በወራሃ የካቲት 23 /1888 ተፃፈ። ስለ አባቱ እና ስለ ልጁ የማይጨነቅ ፍጥረት በቅሎ ብቻ ነው፡፡ ምኒልክን ስታስብ ትናንት አለ፤ በትናንት ውስጥ ዛሬ ይሰራል፤ ታሪክ አመድ አይደለም፤ ረመጥ ነው፡፡ ዛሬን ስትወዝትበት ነገን ያፈላል፡፡ በነገው ስትሰራ ታሪክ ይፃፋል። እኛም እምየ ሚኒሊክ፣ የእቴጌ ጣይቱ እና የአርበኞች አባቶቻችን ልጆቼ በመሆንችን የአባቶቻችን ታሪክ በመጠበቅ የእነሱን ታሪክ ለመድገም ብሎም የተበላሹ ትርክቶችን ለማረም በአባቶቻችን ወኔ ታጥቀን እና ተላበስን በአይናችን 360 ዲግሪ እየቃኘን መሪያችን ወደፊት አስተካከለን ወደከፍታችን እንድንመለስ በዚሁ አጋጣሚ አተማ መልክቱን ያስተላልፋል። ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) በደብረ ብርሀን ቅርጫፍ ጽ/ቤት አስተባባሪነት ይኽን ታላቅ የነፃነት የድል በዓል በደመቀ ሁኔታ ያከበረ ሲሆን “የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ” በሚል መሪ ሀሳብ በአፄ ዘርያቆብ መናገሻ ደብረ ብርሀን ጎዳናዎች ላይ የተለያዩ ትሪኢት በማሳየት እና በዘረያቆብ አደባባይ ደግሞ በሺለላ ፣ ቅርርቶ፣በፍከራ እና በሌሎች ፕሮግራም አክብሮ ውሏል። በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ!! አማራ በከዋክብት ልጆቹ ይደምቃል!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply