
የአማራ አርሶ አደሮች ዛሬም በወሳኝ የስራ ወቅት የአፈር ማዳበሪያ እንዲሰጣቸው በተለያዩ ተቋማት በር በመንከራተት ላይ ይገኛሉ፤ ማህበረሰቡን በኢኮኖሚ ለማዳከም ሲሉ ጸረ አማራ ኃይሎች እየሄዱበት ያለ የሴራ መንገድ ነው ሲሉ ብዙዎች ይናገራሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሀምሌ 3/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በደቡብ ጎንደር፣ በባህር ዳር እና በምንጃር አረርቲ የአማራ አርሶ አደሮች ዛሬም በወሳኝ የስራ ወቅት በየመስተዳድሩ ቢሮ ዙሪያ በመክበብ የአፈር ማዳበሪያ እንዲሰጣቸው በመለመን ላይ ስለመሆናቸው ተገልጧል። በተሉያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የአማራ አርሶ አደሮች በተለይም ካሳለፍነው ግንቦት ወር ጀምሮ የአፈር ማዳበሪያ እጥረት እንዲቀረፍላቸው እንዲሁም ካድሪዎች የቀረበውን ማዳበሪያም ቀጥታ ለገበሬው ከማድረስ ይልቅ ለነጋዴዎች አሳልፈው በመሸጥ በገበሬ ላይ መነገዳቸውንና ብዝበዛ እንዲፈጸም ማድረጋቸውን እንዲያቆሙ በተደጋጋሚ እየጠየቁ መሆናቸው ይታወቃል። ከዚህም አለፍ ሲል በባህር ዳር ከተማ፣ በፍኖተ ሰላም፣ በጃቢህ ጠናን፣ በይልማና ዴንሳ_አዴት፣ በዳንግላ እና በሌሎችም አካባቢዎች አቤቱታው ከፍ ባለ ተቃውሞ መቅረቡ ይታወሳል። ግብር ካልከፈልክ እያለ የሚያስገድደው የክልሉ የዘርፉ አመራርም በሌላ አካል እንደተቀሰቀሰ አድርጎ ቢሳለቅበትም ጅራፍ እያጮኸ የባህር ዳር ከተማ አደባባይን ዙሯል፤ የተቋማትን በር በተደጋጋሚ አንኳኩቷል። በሰላማዊ መንገድ ድምጹን ያሰማው አርሶ አደር ግን ዛሬም ድረስ ተገቢ ምላሽ ባለማግኘቱ በተደጋጋሚ ቅሬታውን በማቅረብ ላይ ይገኛል። ሀምሌ 3/2015 በደቡብ ጎንደር አንዳበት፣ በባህር ዳር እና በምንጃር አረርቲ የአማራ አርሶ አደሮች ዛሬም በወሳኝ የምርት ወቅት በየመስተዳድሩ ቢሮ በማቅናት የአፈር ማዳበሪያ እንዲሰጣቸው በመለመን ላይ ስለመሆናቸው በምስል ተደግፈው እየወጡ ያሉ መረጃዎች የአመልክተዋል። ለገበሬው በወቅቱ ማዳበሪያ አለማቅረብም ማህበረሰቡን በኢኮኖሚ ለማዳከም ሲሉ ጸረ አማራ ኃይሎች እየሄዱበት ያለ የሴራ መንገድ ነው ሲሉ ብዙዎች ይናገራሉ።
Source: Link to the Post