የአማራ ክልሉ የክተት ዐዋጅ

https://gdb.voanews.com/09E98F58-8874-4E98-8BB4-7ED433934F6C_w800_h450.jpg

የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አገኘው ተሻገር በህወሓት ተከፈተ ያሉትን ጦርነት ለመመከት ለሚካሄደውና እና የህልውና ዘመቻ በሚል ለጠሩት ዘመቻ እሁድ ሐምሌ 18/2013 ዓ.ም የክተት ጥሪ አድርገዋል። ፕሬዚዳንቱ ከትናንት በስቲያ/ዕሁድ/ ባደረጉት ጥሪ

“በክልሉ ውስጥ ማንኛውም የመንግሥትንም ሆነ የግል መሳሪያ የታጠቀ እንዲሁም ለግዳጅ ብቁ የሆነ ወጣት ሁሉ ከዛሬ ጀምሮ ይክተት” ብለዋል።

“የትግራይ ሕዝብ ግን ወንድም ሕዝብ ነው” ያሉት አቶ አገኘሁ “ጠላታችን ህወሓት ነው፣ የምንዘምተውም አሸባሪ ቡድኑን ለመመከት ነው” በማለት ተናግረዋል።

ተቃዋሚው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) እና ከፍተኛ የክልሉ የጦር አመራሮችም የክተት ጥሪውን ደግፈውታል። 

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply