የአማራ ክልል መንግስት የፊታችን ረቡዕ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ለተጠራው ሰልፍ እውቅና አለመስጠቱን ገለጸ

የአማራ ክልል መንግስት የፊታችን ረቡዕ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ለተጠራው ሰልፍ እውቅና አለመስጠቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል መንግስት የፊታችን ረቡዕ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና አለመስጠቱን አስታወቀ፡፡

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የፊታችን ረቡዕ ሰላማዊ ሰልፍ መጠራቱን አንስተዋል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ የፊታችን ረቡዕ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የአማራ ክልል እንዲረጋጋ ለማይፈልጉ ሀይሎች ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚመች መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ወቅቱ የተፈጥሮ አዳጋ የተከሰተበት እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ የዓለም አቀፍ አጀንዳ በሆነበት ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህጋዊ አይደለምም ነው ያሉት፡፡

በመሆኑም የክልሉ መንግስት ምንም አይነት ሰልፍ እንዳይካሄድ መወሰኑን ነው አቶ ግዛቸው የገለፁት፡፡

ይህን ተላልፎ ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጣ አካል ካለ ግን የፀጥታ ሀይሉ እርምጃ ይወስዳልም ብለዋል፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

The post የአማራ ክልል መንግስት የፊታችን ረቡዕ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች ለተጠራው ሰልፍ እውቅና አለመስጠቱን ገለጸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

Leave a Reply