የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ነገ ይጀመራል። የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወይዘሮ ፍቅሬ ሙሉጌታ እንደገለጹት፤ ጉባኤው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/bgCUazmumQ7ca70CBKbQfHExH1GHFXgFxpjYJpJrPCnAQXgM2KoZQyDNUYoIMZkKVjBeQAiVE4gAuV82DVglEfEkAdQjQ-u3ehfZd8fAGUeZ-yZEFmIW4OVWgvlP-5dmlBPC1zMcfc75pIY5oKfYuUamwxY2RLLfOGsIeCSlUaY0cN6EeiGpDspnukWdn5kylazRPMtH1yzcN7Var3ceqrNz9F_kf_W5oIs5X8IHiM_o5ejP7ZwJPWHrHUGQSAh8BHEHqsJI_R6RbCgQoBgeG1okSFXby4telLv7AajU4LgR55Acur55v65dot4FJ0Krl3jL6TmZo4tDaxWrkCijWQ.jpg

የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ነገ ይጀመራል።

የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት
የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወይዘሮ ፍቅሬ ሙሉጌታ እንደገለጹት፤ ጉባኤው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ለሶስት ቀናት ይካሄዳል።

በጉባኤው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የአስፈፃሚ አካላት የስድስት ወራት የተጠቃለለ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ሃላፊዋ ጠቁመዋል።

የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎችም በመስክ ያደረጉትን ምልከታ መሰረት አድርገው በሚያቀርቡት ሪፖርት በጥንካሬና ድክመት የተመለከቷቸውን ጉዳዮች ላይ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል።

ምክር ቤቱ በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ሪፖርቱ ይፀድቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል።

እንዲሁም በምክር ቤት አባላት የሚቀርቡ ሌሎች አጀንዳዎች ካሉ ምክር ቤቱ እንደሚወያይባቸውም ወይዘሮ ፍቅሬ አስረድተዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply