የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ በምክር ቤቱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በበጋ መስኖ ስን…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/YTs0Cbg_ifbYO5pd-iEyp0-vxA7J4GsDUc-jtKIEzjj8SHUYQc7O6cA4rrJQUHDsrV-5exfe5OTxBNfNk0jDjqKM6poqckl_dTAajVM4XxTvmP9IpZDSkLwWz_14NmLKpSRLkV8YeCRKoKJYh6YR6aa9rkCQ1gTM5Q6V9s5IRzyh02yQcQEl8uoXo739PoYpRp--RJTVqWe9Z7GBUDkDXm3poHBwd7HnsSQgR3xp7dvjPU4ttLJd0CKAg_r7MCTo2wxMnvpMK7XjotcWVUeLuJ91wY-qgRFM7XM6sA1jLEz9Tp0hcxKje4y8MmWktH5upLVVLYssg3QTd-6YPcvLOw.jpg

የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ በምክር ቤቱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በበጋ መስኖ ስንዴ በአማራ ክልል እየተገኘ ያለው ውጤት እንደ ሀገር ስንዴን ወደ ውጭ ለመላክ የተያዘውን እቅድ እንዲሳካ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

በአማራ ክልል ያለውን እምቅ አቅምና ፍሰት በመጠቀም በበጀት ዓመቱ በምጣኔ ሀብት ረገድ ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች ስለመኖራቸውም ተናግረዋል።
በማእድን ዘርፍ ያለው ጅምርም ተስፋ ሰጪ ነው ያሉት አፈ ጉባኤዋ በኮሮና ወረሽኝ ተቀዛቅዞ የነበረው የቱሪዝም ዘርፉ መነቃቃት መጀመሩንም አመልክተዋል።

ምክር ቤቱ በሁለት ቀን ውሎ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ ሪፖርት ያዳምጣል፣ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የ2014 ዓ.ም በጀት ዓመትና የ2015 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል እንዲሁም የተለያዩ ሹመቶችን ተወያይቶ ያጸድቃልም ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply