አሁን ላይ በአማራ ክልል ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ፣ የኦሮምኛ፣አዊኛ፣ህምጠኛ ፣አርጎብኛ እና አገውኛ ቋንቋዎች የማስተማሪያ ቋንቋ ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ህገመንግስቱ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ባስቀመጠው መሰረት ተግባራዊ ሲያረግ መቆየቱን ተናግረዋል።
ከ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አንስቶ ደግሞ አሁን ላይ የማስተማሪያ ቋንቋ ሆነው በማገልገል ላይ ካሉት በተጨማሪ አዳዲስ ቋንቋዎችን በስርዓተ ትምህርቱ ላይ የማካተት እቅድ መኖሩን ሃላፊው ነግረውናል፡፡
ነገር ግን የትኞቹን ቋንቋ በሚለው ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑንና ገና ከውሳኔ አለመደረሱን ነግረውናል፡፡
የግዕዝ ቋንቋን አካቶ ለማስተማርና ተማሪዎች በግዕዝ ቋንቋ የተፃፉ ቀደምት መፅሀፍትን ማንበብ እንዲችሉና እንዲመራመሩ የማድረግ ሃሰብ እንዳለም ነግረውናል፡፡
ዶክተር ይልቃል እንደሚሉት ግዕዝን በትምህርት ስርዓት ውስጥ ለማካተት መምህራንን ከማሰልጠን ጀምሮ በርካታ ስራዎች ስለሚቀሩ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ መሆኑን አንስተው በቀጣይ አስፈላጊው መሰረተ ልማቶች ሲሟሉ የማስተማር ስራው ይጀመራል ብለውናል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ከአገር ውስጥ ሶማሊኛ ቋንቋን ከዓለም አቀፍ ደግሞ ቻይንኛ ፈረንሳይኛ እና ጀርመንኛ ቋንቋዎችን ለተማሪዎቹ ማስተማር ሊጀምር መሆኑን ማስታወቁ አይዘነጋም።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በትግስት ዘላለም
መስከረም 18 ቀን 2013 ዓ.ም
Source: Link to the Post