የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ የትህነግ እስትንፋስ መመለስ የለበትም ብሏል፡፡ አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 26 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር ትህነግ ከሃያ ዓመታት…

የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ የትህነግ እስትንፋስ መመለስ የለበትም ብሏል፡፡ አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 26 /2013 ዓ.ም ባህር ዳር ትህነግ ከሃያ ዓመታት በላይ ቀንና ሌሊት የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የኖረው የሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ እርምጃ በመውሰድ የሀገር ክህደት ተግባሩን ካወቅን ጊዜ ጀምሮ የክልላችን መንግሥት አስፈላጊውን ሥራ ሲሠራ ቆይቷል፤ በመሥራት ላይም ይገኛል፡፡ ትህነግ የአማራን ህዝብ ጠላት አድርጎ ትግል ከጀመረበትና ሀገር በመምራት ባሳለፋቸው ጊዜያት ሁሉ በሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ላይ አሰቃቂ ግፎችን አድርጓል፡፡ በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ እጅግ አሰቃቂ ግፎችን ፈጽሟል፡፡ ፀረ አማራ የሆኑ ሀሰተኛ ትርክቶችን በመፍጠር ፀረ አማራ የሆኑ ህጎችን አውጥቶ አስፈጽሟል፡፡ ፀረ አማራ የሆኑ ተቋማትን ገንብቶ ከሁለት አሰርት ዓመታት በላይ በአማራ ህዝብ ሰቆቃ ላይ ሲሳለቅ ኑሯል፡፡ ገድሏል፤ ዘርፏል፡፡ የጨለማ እስር ቤቶችን በመላ ሀገሪቱ በድብቅ በመገንባት ከትህነግ ጥይትና ግድያ የተረፈው ህዝባችን ሲሰቃይ ኑሯል፡፡ የግፍ ጽዋው ሞልቶ በአማራውና በመላው የሀገራችን ህዝቦች ትግል የወደቀው አንባገነን ቡድን መንግሥትና ህዝባችን የሰጠውን ሰፊ እድል በንቀት በመተው በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ከየትኛውም ህዝብ ጋር ተከባብሮ የሚኖረው የአማራ ህዝብ ላይ ጅምላ ግድያ እንዲፈጸምበት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ትህነግ በተለያዩ የሀገራችን አካበቢዎች ለፍቶና ሠርቶ የሚኖረው ምስኪኑ የአማራ ህዝብ እንዲታረድ ከፍተኛ ገንዘብና ሎጂስቲክስ በማቅረብ ሀገር የማተራመስ አጀንዳውን ለማስፈጸም ብዙ መስዋእትነት ተከፍሏል፡፡ ብዙም ተጎድተናል፡፡ ነገር ግን ዓላማው እንዳልተሳካ ያወቀው አጥፍቶ ጠፊው ቡድን ይባስ ብሎ የሀገር ህልውናን አደጋ ላይ በመጣል ጦርነት ውስጥ ገብቷል፡፡ ስለሆነም የሀገር መከላከያ ሠራዊት ይህንን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስና የሀገሪቱን ሰላም ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት ትህነግ ዛሬም የአማራን ህዝብ እንደጠላት ቆጥሮ የሚሠራ በመሆኑ ሁሉም አማራ በያለበት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ትህነግ የአማራን ህዝብ የሚያሳዝን ማንኛውንም ነገር ከማድረግ የሚቆጠብ ስላልሆነ ህዝባችን ፋብሪካዎች፣ መሰረተ ልማቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም የመንግሥትና የሀይማኖት ተቋማትን ከፀጥታ ኃይላችን ጋር በመሆን በተጠንቀቅ መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ በየትኛውም የክልላችን አካባቢ የሚኖር ህዝባችን አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኙ የጸጥታ አካላት በማሳወቅ መረጃዎችን ማድረስ ይጠበቅበታል፡፡ ከክልል ጀምሮ እስከ ወረዳ ያለው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መዋቅራችን ኮማንድ ፖስቱ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የሚመለከታቸው የክልላችን አመራሮች የሚሰጡትን መረጃዎች ብቻ ማጋራት ይኖርበታል፡፡ ጦርነቱን በተመለከተ አላስፈላጊ መረጃዎችን ማስተላለፍ ተጠያቂነት ያስከትላል፡፡ የልዩ፣ የፖሊስና የሚሊሻ ኃይላችን በክልሉ ውስጥ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ በአስተማማኝነት እየመራ ያለበት ሁኔታ መኖሩ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም በትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎችም ሆነ በክልሉ የትኛውም ጫፍ የሚገኘው ህዝባችን የክልሉ የጸጥታ ኃይል ለሚያስፈልገው የትኛውም አይነት ድጋፍ ትብብር በማድረግ የተለመደውን ጥረት መቀጠል ያስፈልጋል ሲል የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቀዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply