የአማራ ክልል የሞግዚት አስተዳደር ይብቃ!!! አማራ ለመብትህና ነፃነትህ ታገል!!! – ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም                                                                         

 

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለኮሮናቫይረስ ወይስ ለአማራ ህዝብ!!!

‹‹ያልተረጋጋ ፖለቲካ ባለበት ሁኔታ ቅድሚያ የምትሰጠው የህዝብን ህልውና ነው፡፡ ህልውናው ደግሞ የሚከበረው በሰለጠነና በተደራጀ ኃይል ነው፡፡ ያልተደራጀ ኃይል ህልውና ሊያስከብር አይችልም፡፡ ስለዚህ የተደራጀ የሰለጠነ ኃይል ለአካባቢው ሠላምና ደህንነት ዘላቂ እንዲሆን ያደርጋል፡፡››1 ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ ቃለ ምልልስ የተወሰደ፡፡

 

የኦዴፓ/አዴፓ ብልጽግና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣የፖለቲካ ሴራ

  • ሃገራችንና ህዝብ በኮሮና ቫይረስ ተስቦ በሽታ አንጃቦብን ሳለ ከአዲስአበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ አምስት አውቶቡስ የአማራ ወጣቶች አፍሶ አማራ ክልል ባህር ዳር ማፍሰስ የለየለት ዘረኝነት ሲሆን ፣ ኦዴፓ ብልፅግና መንግስት በኮሮና ቫይረስ ማህበራዊ መራራቅን እየሰበከ በአውቶቡስ ጠቅጥቆ ጭኖ አገር አቆርጦ መሄድ ዜጎች ለመበከል ካልሆነ ምን ይባላል፡፡  በአማራ ክልል  የአስቸኮኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስቱ ለኮሮናቫይረስ በሽታ ማስወገድ ነው፣ ወይስ ለአማራ ህዝብ የሚታገሉ አብን፣ ፋኖ፣ ምሁራንን ለማጥቃት!!!
  • ኢዜማ፣ የንጉስ አጫዋች ሆኖል፣ የኢዜማ ሠይፍ በአንድ በኩል ስለ ዜግነት፣ ብሄራዊነት፣ ህብረ-ብሄርነት ቀን ከሌት በመስበክ ላይ ይገኛል፡፡ ኢዜማ ካድሬዎች ሃገሪቱ በብሄር ብሄረሰቦች የዘር ፖለቲካ እየተናወጠች እያዩ በኦሮሞ ድርጅቶች በኦነግና በኦዴፓ/ ብልፅግና ኦፌኮ ወዘተ መኃል ምንም ልዩነት እንደሌለ፣ በህወኃትና ተቃዋሚዎቹ መኃል የሥልጣን ሹኩቻ በስተቀር ልዩነት እንደሌለ ኤርትራ በርሃ የነበረው ደህሚት፣ በህወኃት ጦርሠራዊትነት ተመልምሎ አብሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ኢዜማን የፈጠረው ግንቦት ሰባት በክህደት ሠራዊቱን በትኖና ትጥቅ አስፈትቶ ለብአዴን ካድሬዎች ቅኝት ባርነት ስር እንዲኖሩ አደረገ፣ ያየገባቸው ታጋዬች ከፋኖ ጋር በመቀላቀል የግንቦት ሰባት ሴራን አጋለጡ፡፡ የኢዜማ ሠይፍ በሁለተኛው በኩል በአማራ ብሄርተንነት የሚደራጀውን መኢአድን፣ አብንና ፋኖን እንዲሁም የወጣት ክንፍ መደበኛ ድርጅቶችን አንገት መቅላት፣ማስመታትና ማሳሰርና ማኮላሸት ተልዕኮ አለው፡፡ የአማራ ክልል የሰኔ 15 የፖለቲካ ሴራ ግድያ ቀጣይ ትዕይንት ኦሮሞዴፓ/አማራዴፓ ብልፅግና አብንና ፋኖን ለመምታት ያቀዱት ሴራ በኢዜማው መሪ ብርሃኑ ነጋና አንዳርጋቸው ጽጌ የሴራ ፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ እኩይ ሥራ ተባርኮ  ተጀምሮል፡፡ ኢዜማ በአማራ ክልል ተወዳድሮ ለማሸነፍ አብን፣ ፋኖና የቀድሞ የግንቦት ሰባት አርበኞች ወዘተ በኦሮሞ ኦዴፓ/ብልፅግና ኮማንድ ፖስት ጦር ሠራዊት መደምሰስ እንዳለባቸው ስምምነት ተደርሶል፡፡
  • ኢዜማ፣ ከአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ የምዕራብ እዝ ጦር ቤዝ የጦር ተዋጊ ጀቶች፣ ታንኮች የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ወዘተ ወደ ኦሮሚያ ክልል ወለጋ ሲዘዋወር ለኦዴፓ/ብልፅግና የፖለቲካ ሴራ አባሪና ተባባሪ በመሆን አብሮ አሲሮል፡፡ ግንቦት ሰባት ኤርትራ በርሃ እያለም በጥቂት ግለሰቦች በተቆቆመ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኦብሳ፣ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) መሪ ሌንጮ ለታ እና ከኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ (ኦብፓ) ሊቀመንበር ብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቹ ጋር በጥምረት ይሠራ የነበረ ድርጅት ነው፡፡ ግንቦት ሰባት ኢዜማን በመመሥረት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር፣ መረራ ጉዲና ጋር እንዲሁም ከዶክተር አብይ አህመድ ኦዴፓ/አዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ጋር በጣምራ በመስራት የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል የሸጠ ድርጅት ነው፡፡ ኢዜማ በእነዚህ የኦሮሞ ድርጅቶች የሃገሪቱ የፖለቲካ በትረ ስልጣን በምርጫ ወይም በሜንጫ እንዲያዝ አብሮ ያሴረ ድርጅት ነው፡፡
  • ኢዜማ፣ በኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪነት ኦዴፓ፣ አዴፓ፣ ደቡብ፣ ሱማሌ፣ አፍር፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሀረሪ ክልል ፓርቲዎችን ፀበል ረጭቶ ከኢህአዴግነት ወደ ብልፅግና ፓርቲን በመቀየረ ፓርቲ ያዋለደ አማካሪ ድርጅት ነው፡፡ ኢዜማ፣ ህወሓት/ ኢህአዴግን የተካውን ኦዴፓ/ ብልፅግና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አገልጋይ ሎሌ በመሆን ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ለሥልጣን እንደማይታገል በአደባባይ የተናገረ ግን በኢዜማ የፓርቲ ፕሮግራም ላይ ለስልያን እንደሚታገል በማስመሰል የገለፀ  መርህ አልባ ድርጅት ነው፡፡
  • ኢዜማ፣ ቁዘማ የሚያደርግበት አብዩት አደባባይ ሃዲያ ሱፐርማርኬት ያለበት ህንፃ ላይ ሁለት ወለል ያለው ትልቅ አዳራሽ፣ መኪኖች፣ ገንዘብ በኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ብልፅግና ተበርክቶለታል::  ዳክተር አብይ የራሱን መፅሃፍ በምን ያህል ኮፒና ገንዘብ እንዳሳተመው በይገለፅም የአንዳርጋቸው ፅጌ መፅሃፍ በ3.5 ሚሊዮን ብር 30 ሽህ ኮፒ አሳትሞለታል፣ መኖሪያ ፎቁን አስመልሶለታል፣ መኪና ሰጥቶታል፣ የቤተመንግሥት የንጉሱ አማካሪነት ብርሃኑና አንዳርጋቸው በቦርድ አባልነት በመሰየም ዳጎስ ያለ ደሞዝ ተቆርጦላቸዋል፡፡ ህዝቡ ለእነሱ  የታለ ደሞዙ ልብሱን የለበሰው ዘፍኖላቸዋል!!!  የዶክተር አብይ የፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ ዋና አማካሪነት አንዳርጋቸውና ብርሃኑ በመንግስታዊና በኢሣት ሚዲያዎች  የዶክተር አብይ አህመድን የኦዴፓ/ብልፅግና የኦሮሞ ዘር ፖለቲካ አራማጅነት በዜግነት፣ በህብረ-ብሄር ፖለቲካ አራማጅ  ነው በማለት ሲምሉና ሲገዘቱ ይውላሉ፡፡ ‹አሣማን ሊፒስቲክ ብትቀባት ያው አሣማ ናት!!!›“You can put Lipstics on a Pig but it is still a Pig!”
  • ኢዜማና ብአዴን/ አዴፓ በአማራ ህዝብ ላይ ከኦዴፓ/ብልፅግና ጋር በመሆን በአብንና ፋኖን ለመደምሰስ ያሴሩት የፖለቲካ ሴራ እንደሚያስጠይቃቸው በመገንዘብ ለማስቆም ወደ ህሊናቸው በመመለስ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ብቻ ችግሩን ለመፍታት የአብይ መንግሥትን በጊዜው እንዲያማክሩ እንጠይቃለን፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአማራ ቴሌቪዝን ማርች 19 ቀን 2020 ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ2 ‹‹ አማርኛ ቆንቆ ተናጋሪ እንጂ አማራ የሚባል ዘር የለም!!! ›› ‹‹እኔ ከአማራ ክልል ውጪ ነው የምኖረው ለምሳሌ ያህል አዲስ አበባ፡፡›› በማለት አዲስ አበባ የአማራ ክልል ውጪ ነው፣ የፌዴራል መንግሥቱ ካላዳነኝ፣የአማራ ክልል ሊያድነኝ አይችልም በማለት ለኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልጽግና ፓርቲ የካድሬነት ሥራውን በመስራት የሽምግልና እንጀራውን እየጋገረ ይቦተልካል፡፡
  • ‹‹ኢዜማ በአማራ ክልል ቢያሸንፍ ህዝቡን ከታች ጀምሮ የስልጣን ባለቤት በማድረግ የአማራን እድገትና ብልፅግና እንደሚያመጡ ተናግረዋል፡፡›› ኢዜማ  አማራ ክልልን ሙጥኝ ያለው ለዚህ ነው፣ በሌሎች ክልሎች በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በደቡብ ወዘተ  የጫማውን አፈር እያራገፉ ያስወጡት የፖለቲካ ሴራውን በማወቃቸው ነው፡፡ በመለስ ዜናዊ ዘመን ብርሃኑና አንዳርጋቸው (የአዲስ አበባ አስተዳደር ፀሐፊ በመሆን ) መለስንና ታምራት ላይኔን ተከትለው ገቡ ብለውም ወጡ፣ የዶክተር አብይ አህመድ መንግሥትን ተከትለው ገቡ ከምርጫው በኃላ ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እነዚህ አዛውንት የፖለቲካ ቁማርተኞች የዲያስፖራውን ገንዘብና እምነት ዘርፈው አገር በመመለስ፣ ዛሬ በአማራ ክልል በአብንና ፋኖ አባላቶች ላይ ለሚፈሰው ደም ተጠያቂ እንደሚሆኑ ጎደኞቻቸውና ዘመዶቻቸው ሊያሳስቦቸው ይገባል እንላለን፡፡
  • ኢዜማ ህወሓት የትግራይ ክልልን ገንጥሎ ፣እስከአፍንጫው ድረስ መከላከያ ሠራዊት ገንብቶ፣ ልዩ ኃይል አሰልጥኖ፣ ሚሊሽያ አስታጥቆየአማራና የአፋር ግዛትን ቀምቶና የደህንነት ኃይሉን ገንብቶ ስውር መንግስት መስርቶ በሰላም እየኖረ የአማራ ክልልን አብንንና ፋኖን ማስመታት የፖለቲካ ስልት ለሚቀጥለው ምርጫ ለኢዜማ ለማመቻቸት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የህዝብ ልጆች የሆኑት የሰማያዊ ፓርቲ (የሽህዋስ አሰፋ)፣ እና የአንድነት ፓርቲ (አንዱዓለም አራጌ) ይሄን አርበኞች ግንቦት ሰባት (ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ) የፖለቲካ ሴራ በማጋለጥ ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን ተወጡ እንላለን፡፡
  • የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞች የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ስር መካለል አለባቸው ብሎ ሲጠይቅ ኦህዴድ/ ኦዴፓ/ ብልጽግና ኢዜማ  ጆሮዳባ ብለዋል፡፡
  • የፌዴራል ፖሊስ ዋና ፅ/ቤት፣ በኦሮሚያ ፖሊስ ዋና ፅ/ ቤቱን አዲስ አበባ ተደርጎል፣ ማዕከላዊ እዙ አዲስአበባ ሆኖ በመላ ኢትዮጵያ ፀጥታ የማስከበር ኃላፊነት ለኦሮሚያ ፖሊስ ተሰጥቶል፡፡ የኦህዴድ/ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የተረኝነት አገዛዝ በአጭር ጊዜ ይገረሰሳል፡፡
  • ኢዜማ ብአዴን/ አዴፓ በአማራ ህዝብ ላይ ከኦዴፓ/ብልፅግና ጋር የፖለቲካ ሴራ በማሴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበረውን የውሃ ካንስትራክሽን አመራር ቡሎ መሻም፣ ኮነሬል አለበል አማረ፣ የመንገዶች ባለሥልጣን አማካሪ፣ ኮነሬል በአምላክ አባይ የገጠር መንገዶች ሥራ አማካሪ ብሎ በመሾም ከሃገር መከላከያ ሠራዊትትና የደህንነት ኃይል እንዲወጡ በማድረግ ጀነራሎቹን ያዋረዱ ‹‹የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ›› መሪዎች አቶ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ተመስገን ጡሩነህ፣ ብናልፍ አንዱአለም፣ ንጉሱ ጥላሁን  ወዘተ የአማራ ህዝብን ጎዶቻችሁን ዶክተር አንባቸው፣ ጀነራል አሳምነው ወዘተ ተገድለው፣ ለስልጣን ፍርፋሪ ንቃችሁ ኦዴፓ/ ብልፅግና የተረኛነት ፖለቲካ ከስሩ ለመመንገል የሚደረገውን ህዝባዊ ትግል ለመቀላቀል ታሪክ ሥሩ እንላለን፡፡ አማራ ክልል፣ ልዩ የፖሊስ ኃይል ሚሊሽያና የደህንነት ሥራ በሌሎች ክልል ሰዎች ተተክቶል፣ ተጨማሪ ስልጠናም በክልሉ ቆሞል፡፡  በኦህዴድ/ ኦዴፓ ብልፅግና እስካልተመነገለ ድረስ አማራ ነፃ አይወጣም እንላለን፡፡ በሌላ በኩል  በኦሮሚያ ክልል የኦሮሚያ ፖሊስ ስልጠና ለ30ኛ ጊዜ በብዙ ሽህዎች ተመርቆል፡፡ ከሜቴክ የ300 ሽህ የክላሽንኮብ  መሣሪያ ከአንድ ሚሊዩን ጥይቶች ለኦሮሚያ ክልል ማስታጠቅ የዘረኝነት ፖለቲካ ለዘር ፍጅት ዝግጅት አንድ እርምጃ መሰናዶ ነው እንላለን ይሄን ድርጊት፣ ብርሃኑም አንዳርጋቸውም፣ አንዱዓለምም፣የሽዋስም ኢዜማም መፅሃፉም ዝም ብሎል፡፡ ለሆዱ ያላደረው የህዝብ ልጅ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ እንዳለው ‹‹ያልተረጋጋ ፖለቲካ ባለበት ሁኔታ ቅድሚያ የምትሰጠው የህዝብን ህልውና ነው፡፡ ህልውናው ደግሞ የሚከበረው በሰለጠነና በተደራጀ ኃይል ነው፡፡ ያልተደራጀ ኃይል ህልውና ሊያስከብር አይችልም፡፡ ስለዚህ የተደራጀ የሰለጠነ ኃይል ለአካባቢው ሠላምና ደህንነት ዘላቂ እንዲሆን ያደርጋል፡፡››  የአማራ ክልል የሞግዚት አስተዳደር ያበቃል !!! አማራ ህዝብ ለመብቱና  ነፃነቱ የአልገዛም የእንቢተኝነት ትግሉን በተደራጀና በሰለጠነ ኃይል ይቀጥላል!!!

 

ምንጭ

  • ‹‹የተነጋገርነው በሙያችን ህዝብን ለማገልገል ነበር…!!››የአማራ ሚዲያ ማዕከል 06 ቀን 2012 ዓ/ም በዩቲዩብ ቪዴዬ ይመልከቱ መታየት ያለበት ነው፡፡
  • “መንግስት ፓስፖርቴን አላድስ በማለቱና እንዳልንቀሳቀስ ስላደረገኝ ነው የእንግሊዝ ዜግነት የወሰድኩት።” አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የአማራ ቴሌቪዝን Premiered Mar 19, 2020 በዩቲዩብ ቪዴዬ ይመልከቱ መታየት ያለበት ነው፡፡ የዶክተር ብርሃኑ ነጋንም መግለጫ ኢዜማን በተመለከተ ይመልከቱ

 

 

Leave a Reply