You are currently viewing የአማራ ክልል  የዳኞች ማህበር የፍርድ ቤቶች እና የዳኞች ትዕዛዝ እንዲሁም ነፃነት  እንዲከበር ጠየቀ!   ሕዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር…

የአማራ ክልል የዳኞች ማህበር የፍርድ ቤቶች እና የዳኞች ትዕዛዝ እንዲሁም ነፃነት እንዲከበር ጠየቀ! ሕዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር…

የአማራ ክልል የዳኞች ማህበር የፍርድ ቤቶች እና የዳኞች ትዕዛዝ እንዲሁም ነፃነት እንዲከበር ጠየቀ! ሕዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ- መስተዳድር፣ ለክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ እና ፖሊስ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግስት አካል እና ባለስልጣን ሆነ ሌላ ተፅዕኖ ነፃ በመሆን የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነፃነትና ገለልተኝነት እንዲያከናውኑ ጥሪ አድርጓል። ፖሊስ የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የፍርድ ቤቱን ነፃነት መጠበቅ እና ማስጠበቅ፣ በፍ/ቤቱ የሚሰጡትን ውሳኔና ትዕዛዝ ማክበርና ማስከበር ዋናኛው ተግባሩና ኃላፊነቱ እንደሆነ የጠቀሰው ማህበሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ስራ:_ 1) ከግለሰቦች ማንነት እና ስራ እንዲሁም ባህሪ አኳያ በመውሰድ፣ 2) ከራሳቸው ግላዊ ፍላጎትና ክብር ጋር በመመዘን የፍርድ ቤቱን ወይም የዳኛውን ትዕዛዝ አለማክበር፣ 3) ትዕዛዙ ከፖሊስ ጋር በተገናኘ ጊዜ ወይም ፖሊስ እንዲታሰር የሚፈልገው ተጠርጣሪ የዋስትና መብት በሚፈቀድለት ጊዜ የታሰረውን ሰው ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆን፣ 4) በታዬ ጊዜ ፍ/ቤቱ የዜጋውን መብት በማስጠበቅ እረገድ በሚሰጠው ትዕዛዝ ምክንያት የፖሊስ አባሉም ሆነ የፖሊስ ፅ/ቤቶች፣ መመሪያዎች/ የተቋቋሙበትን ዓላማ በመዘንጋት የግለሰብ ፖሊስ አባላቱን ፍላጎት ለማስፈፀም የወገንተኝነት ተግባር ይፈፅማሉ፤ 5) ትዕዛዝ የሰጡ ዳኞችንም በማሰር የዳኝነት ሂደቱን አሰራር አስቸጋሪ ሲያደርጉት ይታያል ሲል ገልጧል፡፡ ማህበሩ እንደ አብነት ሲጠቅስም:_ 1) ሰሜን ጎንደር ዞን ዋስትና ለምን ፈቀድክ በሚል በአንድ የልዩ ኃይል አዛዥ ትዕዛዙን የሰጠውን የከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛ ለቀናት መታሰሩ፣ 2) በምዕ/ጎጃም ዞን ዋድ ንዑስ ወረዳ ላይ የፍ/ቤት ትዕዛዝ ባላከበረው የፖሊስ ባልደረባ ላይ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ በመስጠቱ ሌሎች የፖሊስ አባላት ዳኛውን ማሰራቸው፣ 3) በዋግ ኸምራ ዞን ሰቆጣ ወረዳ ፍ/ቤት ዳኛው ዋስትና በመፍቀዱ ምክንያት በዞኑ አስተዳዳሪና ፖሊስ ትዕዛዝ አስተያየት ከሰጠው የዞኑ ዐቃቢ ህግ ጋር ታስረው መቆየታቸው፣ 4) አሁንም በ02/03/2015 ዓ/ም ደግሞ ሰሜን ወሎ ዞን የቡግና ወረዳ ፍ/ቤት ሴት ዳኛ የሆነችው ፖሊስ የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ ባለማክበሩ የገንዘብ መቀጮ በመቀጣቱ ይኸው የፖሊስ አባል ከሌሎች ሶስት ባልደረቦቹ ጋር በመሆን የወረዳ ፖሊስ አዛዥ በሚያውቀው ሁኔታ በዳኛዋ ላይ ያልተገባ ማንገላታትና በመሳሪያ ድብደባ በመፈፀም ፖሊስ ጣቢያ ላይ እንድትታሰር አድርገው ቆይተዋል፡፡ የቡግና ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ጉዳዩን በአግባቡ መምራት ሲገባው ሌሎች የፖሊስ አባላቱ የፈፀሙትን ተግባር መደገፉ ኃላፊነቱን ያለመወጣቱን ያመለክታል ሲል ወቅሷል፡፡ ሌሎች የፖሊስ አባላትም የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ ማክበር እና ማስከበር ሲገባቸው ጥፋተኛ የተባለ የፖሊስ ባልደረባቸው ስለተቀጣ ብቻ ከእርሱ ጋር በመተባብር ዳኛዋን ላልተገባ አንግልት፣ ድብደባና እስር መዳረጋቸው ህጉንና ኃላፊነታቸውን ወደ ጎን በመተው ለስራ ባልደረባቸው ወገንተኝነታቸውን ማሳየታቸው የህግ የበላይነትን አለማክበራቸውና ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆኑን ያልተቀበሉ መሆናቸውን ያሳያል ብሎታል። በመጨረሻም በአጭር ጊዜ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና ጉዳዩን እንዲያውቁት በደብዳቤ ስርኩላር መመሪያ እንዲተላለፍላቸው፣ በረጅም ጊዜ ደግሞ ስልጠና በመስጠት የግንዛቤ ማሳደግ ስራ እንዲከናወን እየጠየቅን፣ መሰል ጉዳዬች እንዲቆሙና እንዲታረሙ ይቻል ዘንድ ድርጊቱን ፈፀሙት የተባሉትን የቡግና ወረዳ ፖሊስ አባላት ላይ ምርመራ ተጣርቶና አስተዳደራዊ ውሳኔ ተሰጥቶ ውጤቱ እንዲገለፅልን አጥብቀን እንጠይቃለን ሲል ማህበሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply