የአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

ሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ማለፊያ ውጤትን ይፋ አድርጓል።

በዚህ መሠረት በ2014 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ማለፊያ ውጤት ለወንዶች 39%፣ ለሴቶች ደግሞ 38% እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች 37% እንዲሆን መወሰኑን ቢሮው አስታውቋል።

በተያያዘ ዜና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪ ምዝገባ ከነሐሴ 23 እስከ ጷጉሜ 4 ቀን 2014 ድረስ ባሉት ቀናቶች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጿል

Source: Link to the Post

Leave a Reply