You are currently viewing የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በገንዘብ ዋስትና እንዲወጡ የመፍቻ ትዕዛዝ የጻፈላቸው የአማራ ፋኖ በባህር ዳር እና የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት እስካሁን አልተፈቱም፤ ከህግ ውጭ አፍነ…

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በገንዘብ ዋስትና እንዲወጡ የመፍቻ ትዕዛዝ የጻፈላቸው የአማራ ፋኖ በባህር ዳር እና የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት እስካሁን አልተፈቱም፤ ከህግ ውጭ አፍነ…

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በገንዘብ ዋስትና እንዲወጡ የመፍቻ ትዕዛዝ የጻፈላቸው የአማራ ፋኖ በባህር ዳር እና የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት እስካሁን አልተፈቱም፤ ከህግ ውጭ አፍነን እንወስዳለን ካሉ አካላት ጋር ፍጣጫ እንዳለ የዐይን እማኞች ተናግረዋል። ሰ.ሜሪካ :- ሐምሌ 23/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሀምሌ 22 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት በተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበውን የክስ መዝገብ ካየ እና ከመረመረ በኋላ በእስር ላይ ያሉ የአማራ ፋኖዎች እያንዳንዳቸው በ25,000 / ሀያ አምስት ሽህ ብር/ ዋስትና እንዲፈቱ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወቃል። እያንዳንዳቸው በ25 ሽህ ብር የገንዘብ ዋስትና እንዲፈቱ የተወሰነላቸው የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላትም ሆነ በተመሳሳይ እያንዳንዳቸው በ20 ሽህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ በችሎቱ የተወሰነላቸው የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አመራሮችና አባላት ከሃምሌ 22/2014 ጀምሮ መፈታት ይችሉ ነበር። ምክንያቱም የተጠየቀውን የዋስትና ክፍያ አጠናቀው አመሻሹን ለማስፈታት ያደረጉት ጥረት መሽቷል ሃምሌ 23/2014 ጠዋት ላይ ይፈታሉ የሚል ምላሽ ከሰባታሚት ማ/ቤት ተሰጥቷቸው ነበር። በዚህም መሰረት ከህግ ውጭ አፍነው ይወስዱብናል በሚል ስጋት ያደረባቸው ባህር ዳርን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የፋኖ ቤተሰቦች እና የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች በተለይም ፍትህ እየተጣሰ ነው በሚል አካሄዱን እየተቃወሙ ያሉ ወጣቶች ሃምሌ 23/2014 ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ገደማ በሰባታሚት ማ/ቤት በር ተገኝተዋል። ይሁን እንጅ በአካባቢው ለአፈና ተሰማርተዋል የተባሉ የአድማ ብተና አባላት “ከዚህ ምን ትሰራላችሁ?” በሚል የፋኖ ቤተሰቦችንና ወጣቶችን ከአካባቢው አሳደዋቸዋል። በመካከላቸው ተፈች ልጆቻችንና ወንድሞቻችን ይዘን እንዳንሄድ ስለምን ትከለክላላችሁ በማለታቸው መካረር እንደነበረ የዐይን እማኞች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል። በማ/ቤትበውስጥ ያሉ ከ2 እስከ 3 ሽህ የሚደርሱ እስረኞችም ከህግ ውጭ ፋኖዎችን አሳፍነን አንሰድም የሚል አቋም መያዛቸው ተሰምቷል። መሃልም በፓትሮል የተጫኑ ባለቀይ ቦኔት የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ማ/ቤቱ በመምጣት የተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በኋላ መመለሳቸው ተሰምቷል። የአማራ ልዩ ኃይል አባላትም ከርቀት እንደሚስተዋሉ ተገልጧል። ይሁን እንጅ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በ20 ሽህ እና በ25 ሽህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ፋኖዎች አልተፈቱም። ቤተሰቦቻቸው፣ የባህር ዳር ነዋሪዎችና የፋኖ አመራሮችና አባላት አሁንም በሰባታሚት ማ/ቤት አካባቢ ሆነው የፋኖዎችን መፈታት እየተጠባበቁ ነው። ከህግ ውጭ የተፈቱ ፋኖዎችን ታርጋ ቁጥሩ በማይታወቅ መኪና አፍኘ እወስዳለሁ የሚልን የማንኛውንም አካል አካሄድ እያወገዙ ይገኛሉ፤ ከአማራ ፋኖዎች ጎን መሆናቸውንም እያሳዩ ነው። ከጎንደር፣ከጎጃም፣ከወሎ እና ከሸዋ ከአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ጋር ቆይታ ያደረጉ ፋኖዎችና የፋኖ ቤተሰቦችም አካሄዱን የለየለት፣ ለምንም ለማንም በዘላቂነት የማይጠቅም የአፈና መንገድ ነው ሲሉ አውግዘውታል። አሁን ላይም የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት በገንዘብ ዋስትና እንዲፈቱ ካዘዘ በኋላ ከባ/ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት 20 የሚሆኑ ፋኖዎችን ከህግ ውጭ እወስዳለሁ ካለ መንግስታዊ አፋኝ ቡድን ጋር ያለው አደገኛ ፍጥጫ እንደቀጠለ ስለመሆኑ ምንጮች አረጋግጠዋል። 1) የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እያንዳንዳቸው የ25 ሽህ ብር ዋስትና በማስያዝ እንዲፈቱ መፍቻ የጻፈላቸውም:_ 1.ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ የአማራ ፋኖ ውህደት አመቻች ኮሚቴ፣ 2.ፋኖ ኢንጅነር በየነ አለማው፣ የአማራ ፋኖ በጎንደር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ 3.ሻለቃ ዳንኤል አስረስ፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፣ የቢትወደድ አዳነ ብርጌድ ዋና አዛዥ፣ 4.ሻለቃ ስጦታው ( የጎቤ መልኬ ታናሽ ወንድም)፣ የጎቤ ብርጌድ አዛዥ፣ 5.ገበየሁ ሞላ የአማራ ፋኖ በጎንደር ሎጅስቲክ ክፍል ኃላፊ፣ 6.ዶ/ር ታደሰ፣ የአማራ ፋኖ በሸዋ አደረጃጀት ኃላፊ፣ 7.አበበ ሙላቱ፣ የአማራ ፋኖ በሸዋ ደ/ብርሃን የምኒልክ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ 8.ኢሳያስ ደመቀ፣ የአማራ ፋኖ በሸዋ ሎጅስቲክ ክፍል ኃላፊ፣ 9.ታደሠ ፍቅረ፣ የአማራ ፋኖ በሸዋ ሰብሳቢ፣ 10.ሽታየ የትዋለ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም የፍኖተ ሠላም ምክትል ሰብሳቢ፣ 11.ጌታሁን በሬ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም የቡሬ ሻለቃ አዛዥ፣ 12.አትንኩት ሠርፀ ድንግል፣ የአማራ ፋኖ ዉህደት አመቻች ኮሚቴ፣ 13.ሰዋሰው አራጋው፣ የአማራ ፋኖ ውህደት አመቻች እና 14.ናትናኤል አበባው፣ የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች ኮሚቴ አባል ናቸው። 2) የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እያንዳንዳቸው የ20 ሽህ ብር ዋስትና በማስያዝ እንዲፈቱ መፍቻ የጻፈላቸው:_ የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት:_ 1) ቴዎድሮስ ጌታቸው፣ 2) መንግስቱ አማራ፣ 3) ማንችሎት እሱባለው፣ 4) ኖላዊት ይልሃል፣ 5) ሀብታሙ ማንደፍሮና 6) ኃይለማሪያም ተባባል ናቸው። የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከአሁን ቀደም በገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የመፍቻ ትዕዛዝ የጻፈላቸውን የባልደራስ ከፍተኛ አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮልን፣ የባህል አስተዋዋቂዋ ትህትና በላይን፣ የአሻራ እና የንስር ሚዲያ ጋዜጠኞችን ከህግ ውጭ አፍነው ወደ ባህር ዳር ማምጣታቸው የሚታወስ ነው። በተያያዘ ከባልደራስ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን ጨምሮ በሌላ መዝገብ የተከሰሱ የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት ሃምሌ 22/2014 በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቀርበው ለሃምሌ 29/2014 ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጣቸው መሆኑ ይታወቃል። © አሚማ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply