የአማራ ክርስቲያንን የግራኝ አህመድ ሰራዊት እንዴት አሸነፈዉ? ይሄዉ ታሪክስ ከዚህኛዉ ዘመን የአማራ ህዝብ መከራ ጋር እንዴት ይሰናሰናል? ———– ሸንቁጥ አየለ ———–…

የአማራ ክርስቲያንን የግራኝ አህመድ ሰራዊት እንዴት አሸነፈዉ? ይሄዉ ታሪክስ ከዚህኛዉ ዘመን የአማራ ህዝብ መከራ ጋር እንዴት ይሰናሰናል? ———– ሸንቁጥ አየለ ——————— ይሄን ጥያቄ የጠየቁት ከዛሬ 500 አመታት በፊት በአማራ ክርስቲያን ላይ የግራኝ አህመድ ሰራዊት መራራ የዘር ፍጅት ሲያደርግ በአይናቸዉ በብረቱ ያስተዋሉ መንፈሳዊ አባት ናቸዉ::እኝህ አባት አባ ባህሪን ይባላሉ:: አባ ባህሪ የአባ ባህሪን ድርሰቶች በሚለዉ መጽሃፋቸዉ የሚገርም ትንታኔ አቅርበዋል:: የአማራ ክርስቲያንን የግራኝ አህመድ ሰራዊት እንዴት አሸነፈዉ? የሚለዉን ጥያቄ ሲመልሱትም:- – “ክርስቲያኑ አማራ በብዙ የስራ ዘርፍ የተከፋፈለ ነዉ:: አንዱ ክፍል ካህን እና መለኩሴ ነዉ::ይሄ ክፍል አይዋጋም::ሌላዉ ክፍል ቀጥቃጭ እና ሸማኔ ነዉ::ይሄም ክፍል አይዋጋም::ሌላዉ ክፍል ደግሞ አዝማሪ እና ዘፋኝ ነዉ::ይሄም ክፍል ጦር በዞረበት ድርሽ አይልም::ሌላዉ ክፍልም መሳፍንት እና ሀብታም ነኝ ባይ ነዉ::ይሄኛዉ ክፍል እጁን ቆሻሻ እንዳይነካዉ ሲጠነቀቅ እና ከወይዛዝርት ጋር ሲላፋ የሚዉል ነዉ:: ሌላዉም ክፍል አፈር ገፊ ነኝ አርሶ በላተኛ ነኝ ብሎ መሬት አለስላሽ እንጅ ጦር የማያዉቅ ነዉ:: ግማሹም የማህበረሰብ ክፍል ሴት ነኝ በማለት በጦር ሜዳ ድርሽ የማይል ነዉ::ሌላዉም ብዙዉ የማህበረሰብ ክፍል ህጻን ነዉ: 18 አመት አልሞላዉም ተብሎ ጦር የማይሰብቅ ነዉ::እንግዲህ ምን ቀረ? የቀረዉ እጅግ ጥቂት የሆነ ተዋጊዉ ሀይል ነዉ::ይሄ ሀይል ቁጥሩ እጅግ ትንሽ ነዉ::እንግዲህ ግራኝ አህመድን የገጠመዉ እና በግራኝ ሀይል የተመታዉ ይሄዉ ሀይል ነዉ::ክርስቲያኑ አማራ ለምን ተሸነፈ ከማለት ይልቅ እንዴት ከምድረ ገጽ አልጠፋም ማለት ይቀላል::ምክንያቱም ግራኝ አህመድ አሰልፎት የመጣዉ ሀይል ብዛቱ እጅግ ብዙ ከመሆኑም በላይ ሴት: ወጣት: አዛዉንት: ሽማግሌ: ጎልማሳ ሳይል እና በስራ ድርሻ ሳይከፋፈል በአንድ ላይ ወደ ጦር የሚተም ሀይልን ነበርና ነዉ” ሲሉ ያብራራሉ:: ———————– እናም የአባ ባህሪን ታሪክስ ከዚህኛዉ ዘመን የአማራ ህዝብ መከራ ጋር እንዴት ይሰናሰናል? ——————————————- -በአሁኑ ዘመን ያሉ የክርስቲያን አማራ ልሂቃን ለነሱ እስከተመቻቸዉ ድረስ ህዝቡን መዉቀስ እንጅ ህዝባቸዉ ላይ የመጣዉን መከራ በጋራ ከህዝብ ጋር ቆሞ ለመቀልበስ አይተጉም:: የስራ ድርሻቸዉ ህዝብ የማያገለግል ምሁርነት የሚመስላቸዉ እጅግ ብዙ ሚሊዮን ልጉማኖች ሞልተዋል -በዚህ ዘመን ጥቂት ሀብት ያፈራ የአማራ ሰዉ ፖለቲካ ሲሸሽ: ሲደበቅ: ልጆቹ ፖለቲካ እንዳይነኩ እንደ ሚሰበር እቃ ሲደባብቃቸዉ እና ከህዝባዊ እዉነት ሲያሸሻቸዉ ይኖራል እንጅ ህብቱን ለህዝብ ጥቅም ስለማዋል ከቶም አያስብም – በዚህ ዘመን ብቻ ሳይሆን በሀይለስላሴም ሆነ በደርግ ዘመን የነበሩት የአማራ ሀብታሞች እና ምሁራን እራሳቸዉም በፖለቲካ እዉቀት ነጻ የሆኑ ልጆቻቸዉንም ከፖለቲካ እዉቀት ነጻ አድርገዉ የሚያሳድጉ ነበሩ::ጠላት እና ወዳጃቸዉን የማያዉቁ ግራ እና ቀኛቸዉን የማያዉቁ ልጆች ::ጥቅት ከተሜነት የቀመሱ እንደሆነ: በተለይም ወደ ሀብታም ሰፈር የተጠጋጉ እንደሆነ ህዝባዊ መከራ እና ሀገራዊ ጉዳይን በአንድ አይናቸዉ በሾርኔ ለማዬት እንኳን የማይደፍሩ የአማራ ምሁራን እና ሀብታሞች እጅግ ብዙ ናቸዉ -የቤተክርስቲያን አገልጋይ ነኝ: ክርስቲያን ነኝ:ካህን ነኝ : ጳጳስ ነኝ : ክርስቲያን ነኝ የሚሉት የዚህ ዘመን ሰዎች እንደ አባ ባህሪ ዘመን ካህናት ሀገር እስኪፈርስ ዝም ብለዉ ዳርዳሩን የሚዞሩ እንኳን አይደሉም::ለጥ ብለዉ የሚተኙ ናቸዉ::ከዚያኛዉ ዘመን የተጨመሩ ክፍሎች ቢኖሩ ክርስቲያን ነኝ የሚሉት ናቸዉ:: -ድግስ ሰባሪ እና እሞቀበት ጨፋሪዎች በዚህኛዉ ዘመን ፖለቲከኞች እንዲሆኑ ተፈቅዶላቸዋል ሳይሆን ሜዳዉ ባዶ ስለሆነ ገብተዉ ይንቦጫረቁበታል -የአማራ ሰዉ እምነቱን ለዉጦ ፕሮቴስታንት የሆነ እንደሆነ ተወዉ::የቀደሙ የአማራ ክርስቲያኖችን ከመርገም እና የዚህ ዘመን የተዋህዶን ክርስትና ከመራገም የዘለለ ምድራዊ ተልዕኮም ያለዉ አይመስለዉም::የግራኝ መሃመድ አይነት ሰራዊት አሁን እደጁም ቆሞ የሚባንን አይደለም:: አባ ባህሪን በዚያ ዘምን በነበሩት ሰዎች ላይ ሲሳለቁ “ሰይፍ አንገታቸዉ ላይ የግራኝ ሰራዊት እያሽከረባቸዉ እነሱ ግን ተዉ አንተ እሱኮ ሰይፍ ነዉ ትቆርጠኛለህ ይላሉ” እንዳሉት አይነት ሰዎች ናቸዉ:: -የአማራ ምሁራን ጥቂት እዉቀት ከዚያም ከዚያም ቀራረዉ የያዙ እንደሆነ መከራ ነዉ::መጥቀስ እና ማጣቀስ ሲያበዙ ጠላት ፊትፊት የማይናገሩ ዝም ብለዉ ግድም ግድሙን የሚሽከረከሩ ሆነዉ ቁጭ አሉ::ኦነጋዉያኑ በመጽሃፋቸዉ ” አማራ እማ ልጅ አልወለደም” ብለዉ እንደተሳለቁት መሆኑ ነዉ -የአማራ ፖለቲከኞች አንዴ ድርጅት ዉስጥ ከተቀረቀሩ በድርጅት ፍቅር ድብን ብለዉ ይታሰራሉ:: አጠቃላዩን የአማራን ህዝብ ጠላት ከማስተዋል ይልቅ በፕሮፖጋንዳ ሲገሻለጡ ቢዉሉ ደስ ይላቸዋል::ልክ በአባ ባህሪን ዘመን እንደነበሩ መሳፍንት የፖለቲካ ድርጅቶች ቅምጣቸዉ በማድረግ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና ቡድኖችን ሲያሽኮረምሙ ዉለዉ ሲያሽኮረምሙ ይሄዉ ሰባ እና ሰማኒያ አመታት አለፉ:: -እርስ በርስ በአሉባላታ ሲጫረስም አሁን ድረስ ባጀ::የግራኝ ማህመድ ሰራዊትን እና የወንድሙን ጸብ ቀላቅሎ እሚተነትን የአማራ ፖለቲከኛ እጅግ ብዙ ነዉ:: – አንዳንዱም የዘመነ መሳፍንት ታሪክ የአማራ የዉድቀቱ ታሪክ መሆኑን ሳያዉቅ በዘመነ መሳፍንት ወቅት የተፈጠሩት ጎንደር: ጎጃም : ሸዋ እና ወሎ የሚባሉት የቀበሌ ስሞች እንደ መለያዉ እየመሰሉት በእነዚህ ከጊዜ ብኋላ በመጡ ልዩነቶች የተነሳ ሲጎናነጥ ይዉላል:: -አሁን ምን ቀረ? ፖለቲካዉ ለማን ተተወ?የዉጊያ አዉዱስ? -አርሶ አደርነቱ እና ስነልቦናዉ በአባ ባህሪን ጊዜ እንዳለዉ ነዉ::የአማራ ሴቶች ስርአት በአባ ባህሪን ጊዜ እንደነበረዉ ነዉ::እንዲያዉም ባላቸዉን ከትግል አዉዱ የሚያርቁት ቁጥር ተበራክቶ እየባጀ ጭምር::ቤት ከሰሩ ሀገር ሲፈር የሚፈርስ የማይመስላቸዉ ሴቶች ቁጥራቸዉ እጅግ በዙ ብቻ ተብሎ የሚተዉ አይደለም:: – አዝማሪዉ እና ዘፋኙም ባህሉም ከቶ አልተለወጠም::እናሳ? ማን ቀረ? እናም የአባ ባህሪን ጥያቄ ለዚህ ዘመንም አማራ ድጋሚ ልትጠዬቅ ይገባል? የአማራ ማህበረሰብ እንዴት እራሱን መከላከል አቃተዉ ብለህ ጠይቅ::ልክ እንደ አባ ባህሪን ትንታኔም አድርግበት:: እናም የአማራ ማህበረሰብ መዳን ከፈለገ አንድ ብቻ አማራጭ አለዉ::ሴት ወንድ ; ምሁር; አርሶ አደር: አንጥረኛ: ነጋዴ: ሀብታም ወጣት : ሽማግሌ ሳይል አብሮ መቆም አለበት:: ሁሉም ወደ ትግሉ አዉድ በጋራ አሸናፊነት ለጋራ ህልዉና የሚል አዋጅ ይመታል:: አማራን ለማደራጀት የተነሳችሁ የፖለቲካ ድርጅቶች ይሄን እስክታደርጉ የአማራዉን ብዙሃን ድጋፍ እንደማታገኙት ማወቅ ይገባል:: በኢትዮጵያዊነት የተደራጃችሁ አማሮችም የአማራን ማህበረሰብ በስፋት አደራጅታችሁ ወደ ትግሉ አዉድ እስክትገቡ ድረስ ብሎም በአማራነት ከተሰለፉት ወንድሞቻችሁ ጋር እስክትናበቡ ድረስ ኢትዮጵያ ብላችሁ ስለተናገራችሁ ብቻ ማንም በቁም ነገር ጆሮዉን ሰጥቶ እንደማያደምጣችሁ ጠንቅቃችሁ ማወቅ ይገባል:: ———- መደምደሚያ ————- የአማራ ማህበረሰብ በዚህ ዘመን የመጣበትን መከራ በመቀልበስ የራሱን ህልዉና ለማረጋገጥ እንዲሁም ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ ከሚፈልጉ ሌሎች ነገዶች ጋር ተባብሮ. ኢትዮጵያን ለመታደግ ከፈለገ ከሁሉ በፊት በራሱ ህብረት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት አለበት። ይሄዉም እስላም ነኝ. ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነኝ፡ ፕሮተስታንት ነኝ፡ ካቶሊክ ነኝ፡ ኢአማኝ ነኝ ፡ የአንድነት ፖለቲካ አቀንቃኝ ነኝ፡ የአማራ ብሄረተኛ ነኝ፡ የዚህ ፓርቲ አባል ነኝ፡ የዚያ ፓርቲ አባል ነኝ፡ ፖለቲካ አልወድም ሳይል እንደ ማህበረሰብ የመጣበትን መከራ በጋራ ቆሞ መመከት አለበት። አማራ የሚባለዉን ማህበረሰብ ለማጥፋት እንደ ፖለቲካ. ግባቸዉ አንግበዉ የተነሱ ሀይሎች አማራዉን በዉስጡ ባሉ አመለካከቶች፡ የስራ ድርሻዎች፡ ወይም መልክና ቁመት ለይተዉ እንደማይተዉት አዉቆ የጋራ ዉስጣዊ ህብረቱ ላይ ቀድሞ መስራት አማራጭ ሳይሆን የህልዉና ጉዳይ ነዉ። እናም የአማራ ማህበረሰብ መዳን ከፈለገ አንድ ብቻ አማራጭ አለዉ::ሴት ወንድ ; ምሁር; አርሶ አደር: አንጥረኛ: ነጋዴ: ሀብታም ወጣት : ሽማግሌ ሳይል አብሮ መቆም አለበት::

Source: Link to the Post

Leave a Reply