You are currently viewing “የአማራ ክብርና ነጻነት በዘላቂነት የሚረጋገጠው በአማራ ሕዝብ የጋራ ትግልና መስዋእትነት ነው!” የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ!  አቶ ግዛቸው…

“የአማራ ክብርና ነጻነት በዘላቂነት የሚረጋገጠው በአማራ ሕዝብ የጋራ ትግልና መስዋእትነት ነው!” የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ! አቶ ግዛቸው…

“የአማራ ክብርና ነጻነት በዘላቂነት የሚረጋገጠው በአማራ ሕዝብ የጋራ ትግልና መስዋእትነት ነው!” የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ! አቶ ግዛቸው በወቅታዊ ጉዳይ ያስተላለፉት መልዕክት! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 8 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የህልውና ዘመቻው በሁሉም ግንባሮች በሕዝባችን ትብብርና የጋራ ተሳትፎ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የትግራይ ወራሪ ኃይል የፈጸመውን ወረራ ለመቀልበስ በክልሉ መንግሥት የቀረበውን የክተት ጥሪ ተከትሎ ሁሉም ሕዝብ በሁሉም የርብርብ ማዕከሎች ለህልውና ዘመቻው የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ነው። ከግንባር ዘመቻው በተጨማሪ በሁሉም የጸጥታ ጉዳዮች ላይ በሁሉም የክልላችን አካባቢዎች ሕዝባችን እያደረገ ያለው ተሳትፎ ወራሪው ኃይል እስኪመነጠር ድረስ ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። የትግራይ ወራሪ ኃይል የአማራን ሕዝብ እንደ ሕዝብ ለማጥፋትና ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከውስጥና ከውጭ ተላላኪ ኃይሎች ጋር ተጃምሎ የሚፈጽመውን ወረራ በጋራ ቀልብሰን ወደ መደበኛው ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብራችን ለመመለስ በጋራ ተቀናጅተን የጀግንነት ተግባር መፈጸም ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም። የአማራ ክብርና ነጻነት በዘላቂነት የሚረጋገጠው በአማራ ሕዝብ የጋራ ትግልና መስዋእትነት ላይ ነው። የኢትዮጵያ ነጻነትም ጸንቶ የሚኖረው ዛሬ በጀግንነት በሚፈጸም ብርቱ ተጋድሎ ነው። ይህን በውል በመረዳት የሀገሩን ክብርና ነጻነት ለመጠበቅ ሁሉም ዜጋ ለህልውና ዘመቻው ባለቤት መሆን ብቻ ሳይሆን በተጠንቀቅ የተዘጋጀ ወታደር መሆን ይኖርበታል። ለጠላት የማንበገር እና ወራሪው ኃይል በገባበት ሁሉ የእግር እሳት እንሁንበት። የሀገር ክብርና ነጻነትም በትውልድ በሚከፈል የጋራ መስዋእትነትና ብርቱ ተጋድሎ እንጂ በነጻ የሚታደል አይደለም። አባቶቻችን ለኢትዮጵያ ነጻነትና ክብር በጋራ በከፈሉት ብርቱ መስዋእትነት በዓለም ሕዝቦች ዘንድ በነጻነት እንድንቆም አድርጎናል። ከራሳችን አልፎ ለአፍሪካ ኩራትና የነጻነት ተምሳሌት የሆነችና ነጻነቷን ያረጋገጠች ሀገር በደምና በአጥንታቸው ክፋይ አቁመው አስረክበውናል። ዛሬም የጀግኖች አባቶቻችን ታሪካዊና ገናና ገድል ለመድገም በእኛ በልጆቻቸው የጋራ ክንድ ላይ ወድቋል። ገድልና ታሪካቸውን ጠብቆ የተከበረችና የታፈረች ሀገር ለትውልድ ለማስረከብ የሚያስችለው የታሪካችን ክፍል በእኛ ሁኔታ ላይ ይወሰናል። ማስቀጠልና ያለማስቀጠል ብቻ ሳይሆን እንደ ሕዝብ የተጋረጠብንን አደጋ ለመቀልበስ በጋራ መነሳት ይኖርብናል። ነጻነታችን እና ክብራችን ለማረጋገጥ በጋራ የምንቆምበት የህልውና ትግል ላይ መሆናችን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም። ሀገር ለማፍረስ እድሜና ጾታ ሳይገድበው፣ ሃይማኖትና የትምህርት ደረጃ ሳይል ወታደር ነኝ ብሎ በጅምላ የመጣን ወራሪ ኃይል ወታደር ሁኖ አከርካሪውን መስበር ያስፈልጋል። ወታደርነት ሙያ ነው፣ ጥበብ ነው፣ ለሀገርና ለሕዝብ ነጻነት ዘብ መቆም ነው። ሕዝብና ሀገርን ከጠላት የሚጠብቁበት ክብርና ጀግንነት ነው። ወታደርነትም በጦር ግንባር ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ተጋድሎ ማድረግ ብቻ አይደለም። ይልቁንስ በየትኛውም መስክ የተሰማራ ዜጋ ሁሉ ለህልውና ትግሉ ድጋፍ ከማድረግ ጀምሮ አካባቢውን ከጠላት ኃይልና ከሰርጎ ገብ በንቃት ለመጠበቅ በተጠንቀቅ በጋራ መቆም ነው። የዛሬና የወደፊት ህልውናችን የሚወሰነውም በእኛ ቅድመ ሁኔታ እና የጋራ ዝግጅት ላይ ነው። ወታደር መሆን በቴክኖሎጂ የረቀቀ ሳይንስ መቅሰም ነው። ወታደር መሆን የሀገርን እና የሕዝብን ነጻነትና ክብር መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የጀግንነት መገለጫ ነው። ያለ ወታደራዊ ሳይንስ ታላላቅ ጀኔራሎች፣ ኮሌኔሎች፣ መኮንኖች ወዘተ. ወታደራዊ መሪዎችን ማግኘት አይቻልም፤ አይታሰብም። ምክንያቱም ወታደራዊ ተቋም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገነባ ግዙፍ ዩኒቨርስቲ ነው። ለኢትዮጵያ ሕዝብ ክብርና ነጻነት፣ ለሀገር ሰላምና ደኅንነት ሲባል በሁሉም መስክ ወታደር መሆን መታደል እንጂ ነውር አይደለም። በውጭና በውስጥ ኃይሎች ቅንጅት ሀገርን ለማፍረስ ወረራ የፈጸመውን የትግራይ ወራሪና አሸባሪ ኃይል ለመደምሰስና ግብዓተ መሬቱን ለማረጋገጥ ሁሉም ዜጋ ወታደር ይሁን ስንል ጦር መሳሪያ ይዞ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ይፋለም ማለታችን ብቻ አይደለም። ጉልበት ያለው በጉልበቱ፣ ምሁራን በእውቀታቸውና በብዕራቸው፣ ሀሳብ ያለው በሀሳቡ፣ ገንዘብ ያለው በገንዘቡ ወዘተ ለህልውና ዘመቻው የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ ከግንባር ዘመቻ ስለማይተናነስ ነው። ስለሆነም ከትግራይ ወራሪ ኃይል ጋር ፊት ለፊት ለሚፋለመው ሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሺያና ፋኖ የሚደረገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማድረግ እንደተጠበቀ ሆኖ ፍላጎቱና አቅሙ ያለው ሁሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊትንና የአማራ ልዩ ኃይልን በመቀላቀል ሀገርና ሕዝብን ከወራሪው ጠላት መጠበቅ ክብርና ጀግንነት መሆኑን መረዳት ይኖርበታል። የአማራ ሕዝብም ሆነ የኢትዮጵያ የወደፊት ህልውና የሚጸናውና የሚወሰነው በአዲሱ ትውልድ ቆራጥነትና ብርቱ መስዋእትነት ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply