You are currently viewing “የአማራ ወጣቶች ሆይ ሙሉ ጊዜያችሁን ወትሮ ዝግጁነት ላይ እንድታደርጉ ስል አማራዊ ጥሪየን አቀርባለሁ።”        በአሸናፊ ገናን አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…   ሚያዝያ 29 ቀን 201…

“የአማራ ወጣቶች ሆይ ሙሉ ጊዜያችሁን ወትሮ ዝግጁነት ላይ እንድታደርጉ ስል አማራዊ ጥሪየን አቀርባለሁ።” በአሸናፊ ገናን አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሚያዝያ 29 ቀን 201…

“የአማራ ወጣቶች ሆይ ሙሉ ጊዜያችሁን ወትሮ ዝግጁነት ላይ እንድታደርጉ ስል አማራዊ ጥሪየን አቀርባለሁ።” በአሸናፊ ገናን አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሚያዝያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ወቅታዊ የአማራ ህዝብ መርህ መደራጄት፣መሰልጠንና መታጠቅ ብቻ ይሁን። ከዚህ ውጭ ምርጫ የለንም። በ 1960 ዎቹ ፖለቲከኞች የተወጠራችሁ ብአዴናዊያን ተውን!! እናንተ በርባኖች ተውን !! ህዝባችን ከትናንት እስከ ዛሬ አውቋችሁ ቢተውም እንደ ጲላጦስ የምትሆኑት ነገር ሰልችቶናል። ክህደታችሁ፣ሆዳምነታችሁ እና አላዋቂነታችሁ ምድር ላይ ወጥቶ ገዝፎ አይተናችኋል። ከእናንተ የምንጠብቀው ፍትህ፣ልማት እና እኩልነት ሞቶ ተቀብሯል። እናንተ ብአዴናውያን ሆይ ከምንስ ተሰራችሁ?? እንዴትስ ተሰርታችሁ ይሆን በጀግናው የአማራ ህዝብ ላይ የምትቀልዱበት?? እንዴትስ ህዝባችሁን ናቃችሁት?? ከትናንት እስከ ዛሬ አማራን ለማዳከም ፣ለመግደል፣ለማፈናቀል እና በሁለንተናዊ ጥቃትስ እንዲጎዳ ይሁንታ ሰጣችሁ?? ስለሆነም ብአዴናውያን ሆይ ከመንገዳችን ላይ ገለል ብትሉ በብዙ ታተርፉበታላችሁና ከመንገዳችን ላይ ተነሱ። ወቅቱ ከስልጣናችሁ ይልቁንስ ወደ ህዝብ መውረድን ይጠይቃል። እናንተ ግን በዛው በሚያቃጥለው ወንበር ላይ ሆናችሁ ምንጊዜም በጠላትነት ፈርጀው ካጠቁንና ከሚያጠቁን ጋር አብራችኋል። እውነት እላችሗል። መንገዳችሁ ሁሉ አረማዊነት ነው። በጊዜ መታረም የማትችሉ ያረጀ ፖለቲካ አራማጆች ሆይ ከፍኖታችን ላይ ተነሱ እንላለን። የአማራ ህዝብ ከብአዴናዊ ብሔርተኞች ራሱን የሚያላቅቅበት ጊዜ ይሄ ጊዜ ነው። የአማራ ህዝብ መዳኛ መንገዱ ላይ ብቻ ያተኩር ።መዳኛው መንገድ ደግሞ ፋኖነት እና አሳምነውነት ብቻ እና ብቻ ነው። የአማራ ፖለቲካ በድንኮች እየተመራ ለውጥ እንደማያመጣ በ31 ዓመቱ ብአዴናዊ ጉዞ ተፈትኖ ወድቋል። ስለዚህ ህዝቤ ሆይ ስለምን ወደ ራስህ አትመለስም?? መፍትሔ ከአጉል ጨዋታ ወጥቶ በራስ አቅም ላይ ተመስርቶ መደራጀት ነው። የእየየ ፖለቲካ፣የጩኸት ፖለቲካ፣የተስፋ መቁረጥ ፖለቲካ ሰባኪዎች ዕርማችሁን አውጡ። በለቅሶ እና ሆይሆይታ የሚመጣ ለውጥ ቢኖር የባለፉት ዘመናት ብዙ ያተርፉን ነበር። ነገር ግን አልተቻለም ይልቁንስ ለገዳዮቻችን ሞራል እና ወኔ ነው የሰጣቸው?? ስለሆነም አማራው ወገኔ ሆይ የመጣህበት ጉዞ አዳጋች እና አድካሚ መሆኑን አውቀህ አዲሱን የትግል ስልት የምታዘምንበት ጊዜው አሁን ነው። የአማራ ፖለቲካ መገኛው የትም የሆነበት ዘመን ላይ ነን። ጫናው ውስጣዊም ውጫዊም መሆኑ ደግሞ ውስብስብ እንዲሆን አድርጎታል። ስለዚህ የትግላችን ቀይ መስመሮችን በጊዜው አስምረን እንደ መታገያ መርህም ልናደርጋቸው ይገባል። አማራው እንደ ባሮክ ከእንቅልፉ እንዲነቃ የአዲሱ ትውልድ ሰራዊት ዋና መርህን ፋኖነት አድርገው። በዚህም ህዝባችን የፋኖ አደረጃጀትን በጥልቀት ገምግሞ መከታው እና ደጀኑ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል። በመሰረታዊነት ፋኖነት የአማራ ህዝብ የከበረ ማንነት ቢሆንም አንዳንዶች በትርክት ስሙን ሊያጠለሹት ይፈልጋሉ። ዕውነታውን ግን ሁሉም የሚያውቀው ሆኖ ፋኖነት በሁላችንም ውስጥ ሰርጾ ገብቷል። ስለሆነም ፋኖን በጠንካራ ድስፕሊን እንዲመራ እና በመርህ እንዲሰራ የሁሉንም ዜጋ ርብርቦብ የሚጠይቅ ነው። በዚህም የተጠናከረ ሁሉንተናዊ ድጋፍ በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፤ ከዚህ አንፃር ፋኖን ማጠናከር አማራን ማዳን ነው ብለን እናምናለን። በነገራችን ላይ አማራነት ወይም ሞት ሲባል የነበረውን ፋኖ በደሙ አፅንቶታል። የነጋዴውንና የልሂቃኑን የውሸት አማራነት አርቆ የቀበረው የእሸቴ ሞገስ እና የይታገስ እሸቴ የተግባር አማራነት ነው። በሌላ መልኩ አማራነትን በልሳንና በቁርባን ካገኙት በላይ በደም ያፀናውን ፋኖን የሚገባውን ክብር አለመስጠት ክህደት እንደሆነ እናምናለን። ስለሆነም የነፍራቃ ፖለቲካ ካድሬዎች የምታደርጉትን እወቁ፣ራሳችሁን ፈትሹ በፋኖ ላይ ጣት የምትቀስሩ ብአዴናዊ ሀገር አፍራሽ ካድሬዎች እረፉ። በአሁናዊ ፖለቲካችን ውስጥ አማራ መሪ የለውም። የአማራ ተወካዮች በሁሉም ዘርፍ ተፈትነው የወደቁ ናቸው። የብልፅግና መንግስት የፀረ አማራ እንደራሴዎችን ጨምሮ ለአማራ ህዝብ ተስፋ የሚጣልባቸው አለመሆኑን የቀን ተቀን ሰላማችን ምስክር ነው። አማራውን ዕረፍት አልባ ያደረገው የብልፅግና መንግስት ስለ ህዝባችን ችግሮች መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ምንጊዜም በጠላትነት ፈርጀው ካጠቁንና ከሚያጠቁን ጋር ተባባሪ በመሆን ለሁሉንተናዊ ጥቃት ተጋላጭ አድርጎናል። የአውዳሚው ድርጅት ክንፍ የሆነው ኦህዴድ እና መሪዎች የህዝባችንን የመከራ ዘመን ለማራዘም በአዲስ ጉልበት እየሰሩ ናቸው። ለዚህም በሁሉም የአማራ ግዛቶች ከታህሳስ ጀምሮ በፈረንሳይ ጀኔራሎች ሰልጥኖ የገባው የደህንነት ክንፍ አማራውን እንደ አዲስ ትርክት በመፍጠር አንድነቱን ለማናጋት ጭምር እየተሰራ ነው። ከዚህ ባለፈ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ዕሳት እየነደደ ስለ ሰላም እና ልማት የሚሰብክ አረማዊ መንግስት ሆኗል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግብፅ፣አሜሪካ፣ደቡብ ሱዳንና ዩጋንዳም እንደ አዲስ ከፀረ ኢትዮጲያ ሀይሎች ጋር በጥምረት እየሰሩ ስለመሆኑም ታውቋል። ስለዚህ የአማራ ወጣቶች ሆይ ሙሉ ጊዜያችሁን ወትሮ ዝግጁነት ላይ እንድታደርጉ ስል አማራዊ ጥሪየን አቀርባለሁ። ፋኖ አማራነትን በደሙ አፅንቶታል!

Source: Link to the Post

Leave a Reply