የአማራ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ወጣት አስናቀ መንገሻ “የአገር ልጅ የማር እጅ” የሚለው የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻን እንደሚቃወም ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 17 ቀን 3013 ዓ…

የአማራ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ወጣት አስናቀ መንገሻ “የአገር ልጅ የማር እጅ” የሚለው የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻን እንደሚቃወም ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 17 ቀን 3013 ዓ…

የአማራ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ወጣት አስናቀ መንገሻ “የአገር ልጅ የማር እጅ” የሚለው የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻን እንደሚቃወም ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 17 ቀን 3013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአማራ ሚዲያ ማዕከል ጋር ቆይታ ያደረገው የአማራ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ወጣት አስናቀ መንገሻ “የአገር ልጅ የማር እጅ” የሚለው የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻን በግሉ የተለያዩ ማሳያዎችን በማንሳት አጥብቆ እንደሚቃወመው ገልጧል። እንደ ወጣት አስናቀ አገላለፅ በአማራ ብሎም በተለያዩ የህ/ሰብ ክፍሎች ላይ በተደጋጋሚ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈፅም የኖረው የህወሀት ነፍሰ ገዳይ ቡድን በቅርቡ በማይካድራና በሁመራ በንፁሀን አማራዎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከፈፀመ በኋላ ሽሽት ያደረገው ወደ ሱዳን መሆኑን አውስቷል። ዛሬ ላይ ሱዳን ለገባው ሳምሪ ለተባለው የህወሀት ገዳይ ቡድን “የአገር ልጅ የማር እጅ” በሚል ስም የድጋፍ ገንዘብ የሚያሰባስቡ አካላት በእጅ አዙር ተዘጋጅቶ ሌላ ጥቃት እንዲፈፅም በፋይናንስ እየደገፉ መሆናቸው መታወቅ አለበት ብሏል። አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ሳይቀር ወደ ሱዳን የተሰደዱት ሙሉ በሙሉ በሚባል አግባብ ወጣቶች መሆናቸውን ያረጋገጠው ጉዳይ ነው ሲል አክሏል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንም በማይካድራ ባሉ አማራዎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈፀመው ከሀዲው የህወሀት ቡድን ባሰማራቸው የልዩ ሀይል አባላት፣ሚሊሻዎችና ሳምሪ በተባለው ኢመደበኛና ገዳይ የወጣቶች አደረጃጀት መሆኑንም ጠቅሷል። በንፁሀን ላይ አሰቃቂ የጅምላ ፍጅት የፈፀመው የነፍሰ ገዳይ ስብስብ በግዳጅ ላይ የተሰማራውን ሀይል ቆሞ እንደማይጠብቅ ይታወቃል ያለው ወጣት አስናቀ ወደ ሱዳን ለመሸሽም ጅኦግራፊያዊ አቀማመጡ ምቹ ስለመሆኑ ገልጧል። ህወሀት ባለፉት 28 ዓመታት ብቻ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈፀም ያቆመ ድርጅት ሳይሆን አሁንም ድረስ የሽብር ተግባሩን አጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ሲያስረዳም እንደአብነት በኦሮሚያ ጉሊሶ፣በደቡብ ጉራ ፈርዳ፣ ኮንሶና አማሮ፣በመተከልና በሌሎች አካባቢዎች በተደረገው የጅምላ ፍጅት ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጁ እንዳለበት የታወቀ ጉዳይ ነው ብሏል። ዘመቻው አድርባይነት የተሞላበትና የሚያስተዛዝብ ስለመሆኑ ሲያስረዳም ከአሁን ቀደም በፅንፈኞች ያለቁ ዜጎችና በሚሊዮን የሚቆጠሩ የተፈናቀሉ ወገኖች ባሉበት ሁኔታ አሁን ላይ ይህ ዘመቻ መጀመሩ አሳፋሪና አሳዛኝ ነው ብሏል። ወጣት አስናቀ ሲቀጥልም በቅርቡ በግፍ የተጨፈጨፉ የመከላከያ ሰራዊት ቤተሰቦችን ወይም ማይካድራ ላይ የተረሸኑትን ከ600 በላይ የሚሆኑ ንፁሀን ቤተሰቦችን የዘነጋ፣ ይልቁንስ በጥይት፣በገመድ አንቀውና በስለት ገድለው ለሸሹ አካላት እርዳታ መጠየቅ ከህግም ሆነ ከሞራል አንጻር ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም ሲል አውግዟል። በመሆኑም ሆንተብሎ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በጅምላ የዘር ፍጅት በመፈፀም ለሸሹ ወንጀለኞች “የአገር ልጅ የማር እጅ” በሚል የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ ያሉ አርቲስቶችም ሆኑ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸው እስካልተቆጠቡ ድረስ በተባባሪነት ከተጠያቂነት አያመልጡም ብሏል። መንግስት ማድረግ ያለበትም ሱዳን ላይ የተጠለሉ ነፍሰ ገዳዮችን በህግ ተጠያቂ የሚያደርግበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለበት፣ መሳሪያቸውን የት እንደቀበሩት መመርመር እንዲሁም አንሰራርተው ሌላ ጥቃት እንዳይፈፅሙም ህዝቡ መጠንቀቅ አለበት ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል። ከአማራ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ከወጣት አስናቀ መንገሻ ጋር ያደረግነው ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply