
የአማራ ወጣቶች ማህበር ስራ አስፈፃሚ ወጣት ሰሎሞን ልመንህ በገዢው ቡድን አፋኝ የፀጥታ አካላት መታፈኑን አረጋግጠናል ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) አስታወቀ ‼️ መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአማራ ወጣቶች ማህበር የአደረጃጀት ጉዳይ ስራ አስፈፃሚ ወጣት ሰለሞን ልመንህ በቀን 22/07/2015 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ከሌሊቱ 5:00 ሰዐት ላይ የፀጥታ ልብስ በለበሱ ሰዎች ታፍኖ መወሰዱን እና ሜኪሲኮ አካባቢ በሚገኘው የገዢው ቡድን ማጎሪያ ካምፕ እንደሚገኝ መረጃ ደርሶናል ። የአማራ ወጣቶች ማህበር ባደረገው የተወሰነ የማጣራት ተግባራት የስራ አሰፈፃሚ አባላችን ያለበት ሁኔታ እጅጉን ያሳስበናል ።በቅርብ ቤተሰቦቹ ላይ የደረሰው ያለበትን ሁኔታ አለማወቅ የተፈጠረ እጅግ ዘግናኝ እና አስቸጋሪ ስነ – ልቦናዊ የመረበሽ ስሜት ውስጥ እንደሚገኙ አረጋግጠናል ።ይህ ግፍ ተገቢ ያልሆነ ፣የስርዓተ መንግስቱ አማራ ጠልነት አንዱ እና ትንሹ ማሳያ ነው ። በማሰር ፣በማዋከብ የሚቆም የአማራ ትግል የለም ።የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ። ህልውናችን በክንዳችን‼️ የአማራ ወጣቶች ማህበር (አወማ) “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post