የአማራ ወጣቶች ማህበር በመካነ ሰላም አባል የሆነው መምህር ተሾመ ዳኜ በጥይት መገደሉ ታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

የአማራ ወጣቶች ማህበር በመካነ ሰላም አባል የሆነው መምህር ተሾመ ዳኜ በጥይት መገደሉ ታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር በመካነ ሰላም አባል የሆነው መምህር ተሾመ ዳኜ ባልታወቁ ሰዎች በጥይት መገደሉን ማህበሩ አስታውቋል። ስርአተ ቀብሩም በመካነ ሰላም ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ዘመድ ወዳጆቹና የከተማችን ነዋሪ በተገኘበት የተፈፀመ ሲሆን ገዳዩ እስካሁን ሊታወቅና ሊያዝ አልቻለም ተብሏል። በመምህሩ ህልፈትም የአማራ ማህበር በመካነ ሰላም አባላትና አመራሮች እጅጉን ማዘናቸውን የገለጸው ማህበሩ ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጆቹ ሁሉ መፅናናትን ተመኝቷል። መምህሩ አገር አማን ብሎ ሲንቀሳቀስ በነብሰ ገዳይ እጅ ወድቋል። የፀጥታ አካላት ወንጀለኛውን ተከታትለው ለፍርድ እንድያቀርቡ ማህበሩ አሳስቧል። መላው አባላትም ፍትህ በመጠየቅ የወንድማችንን ገዳዮች ለፍርድ በማቅረቡ ሂደት ድምፅ እንድትሆኑ ጥሪ ስለመቅረቡ የአማራ ወጣቶች ማህበር በመካነ ሰላም አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply