የአማራ ወጣቶች ማህበር በምዕራብ አውስትራሊያ አመራሮችና አባላት በከሃዲው ትሕነግ ላይ ተገቢ ህግ የማስከበር እርምጃ በመውሰድ ወልቃይት፣ጠገዴ፣ጠለምትና ራያ ነጻ እንዲወጡ ያደረጉ ጀግኖችን አ…

የአማራ ወጣቶች ማህበር በምዕራብ አውስትራሊያ አመራሮችና አባላት በከሃዲው ትሕነግ ላይ ተገቢ ህግ የማስከበር እርምጃ በመውሰድ ወልቃይት፣ጠገዴ፣ጠለምትና ራያ ነጻ እንዲወጡ ያደረጉ ጀግኖችን አመሰገኑ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በውጭ ሀገር ሆነው በተለያዩ በጎ አድራጎት ተግባራት ከተሰማሩት እና የአማራው ቱባ ወግ እና ባህሉ፣ ታሪኩና እሴቱ ጎልቶ እንዲወጣና በሌሎች ዘንድም እንዲታወቅ በማድረግ በኩል የድርሻቸውን እያበረከቱ ከሚገኙት አማራዊ አደረጃጀቶች መካከል የአማራ ወጣቶች ማህበር በምዕራብ አውስትራሊያ አንዱ ነው። በቅርቡ ለወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ 94,500 ብር እንዲሁም ለአማራ ልዩ ሀይል፣ለፋኖ፣ለሚሊሻውና ለመከላከያ ሰራዊት በሚልም በአውስትራሊያ ከአማራ ማህበር ጋር በመተባበር ከበጎ ፈቃደኞች በማሰባሰብ 530 ሽህ ብር ድጋፍ ያደረገ ስለመሆኑ ከማህበሩ ሊቀመንበር ወጣት ኤርሚያስ መኳንንት የተገኘው መረጃ አመልክቷል። በትናንትናው እለት ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም በአማራ ወጣቶች ማህበር አስተባባሪነት አመራሮችና አባላቱ እንዲሁም በምእራብ አውስትራሊያ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች፣ ተጋባዥ የኢትዮጵያ ኮሚቴ አባላት፣ የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት እና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በአውስትራሊያ ፐርዝ በተገኙበት እብሪተኛውን ትሕነግ ያንበረከኩ ጀግኖችን አመስግነዋል። ለትግሉ የራሱን ድጋፍ ሲያደርግ የቆዬው የአማራ ወጣቶች ማህበር በምዕራብ አውስትራሊያ በከሃዲው ትሕነግ ላይ ተገቢ ህግ የማስከበር እርምጃ በመውሰድ ወልቃይት፣ጠገዴ፣ጠለምትና ራያ ነጻ እንዲወጡ ላደረጉ ጀግኖች ያላቸውን ክብርና ምስጋና በሻማ ማብራት፣ በሕሊና ፀሎት፣ በስነ ጹሁፍ፣ በውይይትና በመሰል ልዩ ልዩ ዝግቶች ገልፀዋል። በግዳጅ ቀጠናው ተሰልፈው በዘር ማጥፋት ወንጀል የተሰማራውን የትሕነግን ቡድን ድባቅ ለመቱት የአማራ ልዩ ሀይል፣የአማራ ፋኖ፣የአማራ ሚሊሻዎችና የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ላቅ ያለ ክብርና ምስጋና እንዳላቸው አስታውቀዋል። ግፈኛው እና ተስፋፊው ትሕነግ ከልማት ይልቅ ለዓመታት በወልቃይት፣ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ ሲገነባቸው የከረሙ አያሌ ምሽጎችን በመደርመስና አሸባሪውን በመደምሰስ ወቅት የተሰው ጀግኖችን ጨምሮ በማይካድራና በሌሎችም አካባቢዎች በቡድኑ ለተጨፈጨፉ አማራዎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘንም ጥቁር ቲሸርት በመልበስ ገልፀዋል። “አማራ” የሚል ቲሸርት በመልበስ በምስጋና እና በመታሰቢያ ዝግጅቱ ከተገኙትም በርካቶች በአውስትራሊያ ተወልደው ያደጉ አማራዎች ስለመሆናቸው በውስጥ ለአሚማ የደረሰው መረጃ አመልክቷል። በምስጋና እና መታሰቢያ ዝግጅቱም የአማራ ወጣቶች ማህበር በምዕራብ አውስትራሊያ ሊቀመንበር ወጣት ኤርምያስ መኳንንት ተገኝቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል። ያስተላለፈው ሙሉ መልዕክትም የሚከተለው ነው:_ በመጀመሪያ ይህን ቀን በአንድላይ አሰባስቦ ላገናኘን ሃያሉ እግዛብሄር ክብር እና ምስጋና ይድረሰው። በመቀጠልም ጥሪአችንን አክብራችሁ ለተገኛችሁ እንግዶቻችን በሙሉ በእኔ እና በባልደረቦቸ በአማራ ወጣቶች ማህበር አባላት ስም ምስጋናየን ከልብ አቀርባለሁ። የአማራ ህዝብ ላለፉት አርባ አምስት አመታት (45 ) በትህነግ የፀረ-አማራ ስራዓት የከፋ አገዛዝ ግፍ ቀማሽ ሁኖ ቆይቷል ፣ እንዲሁም መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት የዚሁ እጣ ፈንታ ባለቤት ሁነው ይኖሩ ነበር። በመሆኑም ይህን ማብቂያ የሌለው የጥፋት ዘመቻ ህዝባችን እንደምታዉቁት ለዘመናት ያለእረፍት ሲታገል ቆይታል። ይህ ግፍ ሰርቶ እና ገድሎ የማይጠግበው ፀረ-አማራ ስርዓት ባለፉት አራት ሳምንታት ይባስ ብሎ በታሪካችን ታይቶ እና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ በአማራ ህዝብ እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ እንደለመደው የግፍ ጭፍጨፋ ፈፀሞባቸዋል። በዚህም የተነሳ ይህን ጨካኝ ፣ አረመኔ ፣ ግፍ ሰሪ እና ገዳይ የሆነውን ስርዓት ጀግናው የአማራ ልዩ ሀይል ፣ የአማራ ሚኒሻ ፣ የአማራ ገበሬ ፣ አይበገሬው ህዝባዊ ሃይሉ ፋኖ ፣ የአፋር ልዩ ሀይል ፣ የአፋር ሚኒሻ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ይህን አሸባሪ ስርዓት ላይመለስ እስከወዲያኛው ሸኝተውታል። በመሆኑም ይሄን የግፍ ስርዓት እንዳልነበረ ለማድግረግ መስዕዋት ለሆኑት እና ለታገሉት ጀግኖቻችን መጠነ ሰፊ ክብር እና ምስጋና በማቅረብ ደስታችንን ለመግለፅ ይሄው ዛሬ በዚች ቀን በአንድላይ ተሰባስበናል እንኳን ደስ አላችሁ፤ አለን። በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ። የአማራ ህዝብ በታሪኩ ለነፃነቱ እና ለአንዲት ኢትዮጵያ ሃገሩ ሉአላዊነት ከሌሎች ሃገር ወዳድ ህዝቦች ጋር ሁኖ ተደራድሮ አያቅም። በታሪክ የተፃፈለት ይህ ትልቅ ህዝብ አሁንም ለሃገር እና ለህዝቡ የቆመ መሆኑን ለአብነት በፀረ-አማራው እና በሃገር አፍራሹ ትህነግ በዳንሻ ተከበው የነበሩትን የህዝብ ልጆች የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊት የሞት ድግስ ቀድሞ በመድረስ ያከሸፈው ይህ የነፃነት ባለቤት የሆነው እና ሃገር ሰሪው አማራ ነው። በመሆኑም ነፃነታችን ለማረጋገጥ እና ህዝባችንን ለማዳን ከእስከ ዛሬው በበለጠ እና በተጠናከረ መልኩ መስራት እንደሚጠበቅብን ለሁሉም ውድ የአማራ ልጆች እና ለሌሎች ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን እህት ወንድሞች በምእራብ አውስትራሊያ በአማራ ወጣቶች ማህበር ስም ማሳወቅ እፈልጋለሁ፣ ይህ ወንጀለኛ ቡድን በአገር አቀፍም ሆነ በአለም አቀፍ ደርጃ በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ በሚል የሚከተሉትን ነጥቦች እናቀርባለን። 1) ትህነግ ከሰላማዊ ድርጅት እንዲሰረዝ እና በአሸባሪነት እንዲፈረጀ 2) ትህነግ በአለም አቀፍ የሽብር ክስ እንዲከሰስ 3) ትህነግ ለአለፉት አርባ አምስት አመት ሙሉ በአማራው ላይ ላደረገው የዘር እልቂት እንዲጠየቅ 4) በሰሞኑ በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን መጠነ ሰፊ ጥቃት እና እንዲሁም በማይካድራ በአማራ ልጆች ከ600 በላይ ጭፍጨፋ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ እና ወንጀለኞች ለህግ እንዲቀረቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ብሏል። የአማራ ወጣቶች ማህበር በምዕራብ አውስትራሊያ አስተባባሪነት የተዘጋጀው የምስጋና እና የመታሰቢያ ዝግጅትን በአሚማ የየቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply