የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን አስቸኳይ ጥሪ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከ…

የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን አስቸኳይ ጥሪ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ለተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ:_ ጉዳዩ፦ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈፀሙ የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ አስፈላጊው ምርመራ ይደረግልን ስለማለት። በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ወለጋ በተባለ ቦታ ላለፉት 4 ዓመታት በርካታ አሰቃቂ ወንጀሎች ተፈፅመዋል። ራሱን መንግስት ብሎ የሚጠራዉ አካል በተደጋጋሚ ለዚህ ድርጊት እንደመደበቂያ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዳይካሄድ የማይፈልጉ አካላት ናቸው የሚል ስላቅ ከምርጫዉ በፊት ይሰጥ ነበር። ምርጫዉ ከተገባደደም በኃላ ይህ ጭፍጨፋ እንደቀጠለ ነው። ለዚህም ማሳያ ቅዳሜ ሰኔ 11/2014 ዓ.ም በተፈፀመ ጥቃት በ1ቀን 1500_3000 የሚደርሱ ንፁሀን አማራወች መጨፍጨፋቸው መረጃዎች ያሳያሉ የቁጥር ልዩነት ከምርመራ በኋላ ይፋ የሚሆን ቢሆንም። በመቀጠልም ሰኔ 27/2014 ዓ.ም በ1 ቀን ዉስጥ ከ600 በላይ ንፁሀን መጨፍጨፋቸውን እንገልፃለን። ይህ ከላይ የቀረበው ቁጥር በአንድ ወገን ላይ ማለትም በአማራ ህዝብ ላይ የተፈፀሙ በመሆናቸው ጥቃቱ ሆን ተብሎ የተፈፀመ መሆኑን ያሳያል። ይህን ችግር ከመፈፀሙ በፊት በተደጋጋሚ ነዋሪዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝቦች ጭምር አቤቱታቸው መንግስት ለሚባለዉ አካል ቢያሰሙም ምንም አይነት መፍትሄ አልተገኘም። ስለዚህ ማህበራችን የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ገዥው መንግስት ምንም አይነት መፍትሄ ስላልሰጠን ጉዳዩ በአለም አቀፍ ደረጃ በገለልተኝ አካል እንዲታይልን እናሳስባለን። የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ደብረብርሀን ሐምሌ 21/2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply