You are currently viewing የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ   ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በፃፈው ደብዳቤ ከአሸባሪው ህወሃት ትህነግ ጋር የሚደረገው ድርድር የአማራንና የአፋርን ህዝብ እረፍት የሚነሳ መሆኑ እንዲታይ…

የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በፃፈው ደብዳቤ ከአሸባሪው ህወሃት ትህነግ ጋር የሚደረገው ድርድር የአማራንና የአፋርን ህዝብ እረፍት የሚነሳ መሆኑ እንዲታይ…

የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በፃፈው ደብዳቤ ከአሸባሪው ህወሃት ትህነግ ጋር የሚደረገው ድርድር የአማራንና የአፋርን ህዝብ እረፍት የሚነሳ መሆኑ እንዲታይ? ሲል ጠየቀ። የአማራ ሚዲያ ማእከል መስከረም 6 2015 ዓ/ም … አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የፃፈው ደብዳቤ እንደሚከተለው ነው። ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር በማለት እራሱን የሚጠራው ቡድን በትግራይ ክልል ተደብቆ በርካታ የሽብር ሴራዎችን ሲያሴር ቆይቶ የሽብር ስራውን ሀገር በመካድ ሀ ብሎ የትግራይ እናቶችን፣አባቶችን ሲረዳ ውሎ ደክሞት ወደ ማረፊያው የገባው የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊትን በመውጋት መጀመሩ “ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ሀቅ” ነው። ይህ ቡድን በስልጣን በቆየባቸው 27 አመታት ነገድን ያተኮረ የጥላቻ ዘር በመዝራት የስልጣን ጊዜውን ሲያራዝም የኖረ ለሀገር ክብር ለሀገር ሉዓላዊነት ምንም አይነት ደንታ የሌላቸው ግለሰቦች ስብስብ ነው። የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመው አስነዋሪ ክህደት የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ወደ ጎን ትቶ ይቅር ቢባልም አሻፈረኝ በማለት ለሁለተኛ ጊዜ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ላይ ጦር አዝምቷል፣ንፁሃን ገድሏል፣የሀገር መከላከያ ስራዊት ላይ የስልጣን ጥሙን ለማርካት ቃታ ስቧል። ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ላይ ሲያደርግ የነበረው ግፍ ህዝባችንን ወደ ምሬት በመክተቱ በህዝቦች ጠንካራ ትግል ተመክቶ ወደመጣበት ተመልሶ ዳግም የይቅርታ እጅ ቢዘረጋለት አሻፈረኝ በማለት መልሶ ለሶስተኛ ጊዜ ጦርነት አንስቷል።ሆኖም ግን በሁሉም አቅጣጫ ያሰበው ስላልሆነ አሁን ድርድር በማቅረብ ተበዳይ ለመምሰል እየጣረ ይገኛል ይህ ሃሳብ ምንም አይነት ተቀባይነት አይኖረውም። “ቢሆንም ይገለባበጣል በዳይ ተቀምጦ ተበዳይ ይቀጣል”! እንዳሉት አበው ለሊቃውንት በብልፅግና ፖርቲ እና በአሸባሪው ህውሀት/ትህነግ/ የሚካሄድ ድርድር ዘለቄታዊ መፍትሄ ሊያመጣ ስለማይችል ሁሉን ያማከለ ማለትም ከአማራ ወጣቶች፣ከተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች እስከ ሀገር ሽማግሌዎች ድረስ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ድርድር እንደሚያስፈልገው የአማራ ወጣቶች ማህበር በሽዋ ፅኑ አቋም አለው። ነገር ግን በዚህ መልክ የማይሄድ ድርድሮች የአማራን፣የአፋርን እና መላው የኢትዮጵያ ህዝብን መካድ የሚሆን ስለሆነ ድርድር የሚባል ሀሳብ እና መደራደር እፈልጋለሁ ካለ ለትግራይ ንፁሃን እናቶች፣ለትግራይ ንፁሃን አባቶች፣ወንድሞች ፣እህቶችና ህፃናት ሲባል ቡድኑ ማድረግ ያለበት ጉዳዮች፦ 1,በዋናነት ይህ አሸባሪ ቡድን ሀገር ለመበትን አልሞ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን እንደራደር የማለት ሃሳብ ካለው ማንኛውም ሰላማዊ ቡድኖች እንደ ሚያደርጉት ሀሳቡን ፍላጎቱን ትጥቁን ፈቶ በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ፤ 2,በወረራ የያዛቸውን የአማራና የአፋር እርስቶች ከሁሉም ቦታ ለቅቆ መውጣት 3,ለፈፀመው የሀገር ክህደት የኢትዮጵያ ህዝብ በዋናነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ይቅርታ እንዲጠይቅ ለሟች ቤተሰብ ካሳ በመክፈል የህዝባችን ፍትህ እንድረጋገጥ ያስፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ ውጭ የሚደረጉ ድርድሮች የአማራን፣የአፋርን በተጨማሪም የትግራይን ህዝብ ለበለጠ ችግር መከራ፣ስቃይ እና እልቂት የሚዳርጉ በመሆናቸው ንፁሃን የትግራይ ተወላጆች ቡድኑ ከሚገኝባቸው ቦታዎች እራሳቸውን እንዲያርቁ እና በዚህ አሸባሪ ላይ እስከ መጨረሻው እርምጃ መወሰድ አለበት። በጥምር ጦሩ ስር ለሚገቡ የትግራይ ተወላጆች ህዝባችን አስፈላጊውን እገዛ እና እንክብካቤ እንደሚያደርጉላቸው ያለንን ፅኑ እምነት እየገለፅን ከላይ ከተጠቀሱት ውጭ የሚደረግ ማንኛውም ድርድር በአማራ ህዝብ ተቀባይነት አይኖረውም ስንል እናሳስባለን ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ በፃፈው መግለጫ አሳውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply