You are currently viewing የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን ችሎት ለመከታተል በፍ/ቤት ለተገኙ በርካታ የባህር ዳር ነዋሪዎች “ክብር ይገባችኋል!” ሲል ምስጋና አቀረበ።  አማራ ሚዲያ ማዕ…

የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን ችሎት ለመከታተል በፍ/ቤት ለተገኙ በርካታ የባህር ዳር ነዋሪዎች “ክብር ይገባችኋል!” ሲል ምስጋና አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕ…

የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን ችሎት ለመከታተል በፍ/ቤት ለተገኙ በርካታ የባህር ዳር ነዋሪዎች “ክብር ይገባችኋል!” ሲል ምስጋና አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፏል:_ ክብር ይገባችኋል!! በመጀመሪያ በዛሬው ዕለት ህዳር 12/2015 በባህር ዳር ከተማና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት የጀግናው ፣የምልክታችን እና የመሪያችን ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን ችሎት ለመከታተል በፍ/ቤት ለተገኛችሁ በርካታ የከተማችን ነዋሪዎች እንዲሁም ከሰባታሚት ማረሚያ ቤት ወጦ ፍ/ቤት ደርሶ እስኪመለስ አስፈላጊውን ክትትል ላደረጋችሁ የከተማችን ንቁ ወጣቶች በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋና በአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር ስም ይድረሳችሁ ። የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ክርክርን በሚመለከት ጠበቆች ባቀረቡት የክስ መቃወሚያ አግባብ ጉዳይ “ክሱን ውድቅ ለማድረግ” ወይም ደግሞ “ክሱ በቀረበበት አግባብ ክርክሩ ይቀጥል” ለማለት ፍርድ ቤቱ ለመጭው ህዳር 16/03/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ቀጥሯል። በመሆኑም በመጪው አርብ ማለትም በ16/03/2015 ዓ.ም እንደተለመደው በባህር ዳር ከተማና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት በመገኘት ለምልክታችንና ለመሪችን ያለን አማራዊ ወዳጅነት ፣ፍቅር ፣አንድነት እንዲሁም ፍፁማዊ ህብርት እንገልፅ ዘንድ ጥሪያችን እናስተላልፋለን ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply