You are currently viewing የአማራ ወጣቶች ማህበር በፍኖተሰላም  ያስተላለፈው አስቸኳይ መልዕክት ‼️ ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ባህርዳር  'ህዝብን ከመንግስት የመነጠል ስራ ሰርታችኋል' በሚል በአገዛዙ…

የአማራ ወጣቶች ማህበር በፍኖተሰላም ያስተላለፈው አስቸኳይ መልዕክት ‼️ ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ባህርዳር 'ህዝብን ከመንግስት የመነጠል ስራ ሰርታችኋል' በሚል በአገዛዙ…

የአማራ ወጣቶች ማህበር በፍኖተሰላም ያስተላለፈው አስቸኳይ መልዕክት ‼️ ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ባህርዳር ‘ህዝብን ከመንግስት የመነጠል ስራ ሰርታችኋል’ በሚል በአገዛዙ በግፍ እስር ላይ የሚገኙት ወንድሞቻችን የፊታችን ሀሙስ ፍ/ቤት ይቀርባሉ ። የታሰሩ ልጆቻችን፦ 1- ፲ አለቃ ገበያው አበረ 2- ምህረት አያሌው 3- ዉበቱ አላምረው 4- እንዳሻው መስፍን፣ ሲሆኑ፥ የታሰሩበት ሰበብም ‘ህዝብን ከመንግስ የመነጠል ስራ ሰርታችኋል’ የሚል ተልካሻ ምክንያት ነው ብሏል የወጣት ማህበሩ። ፃዕረ ሞት ላይ ያለኸው ብአዴን/ ብልፅግና፣ ከህዝብ የተገለልከው፣ ታጥቦ በማይፀዳው አድርባይነህ ፣ሎሌነትህ እና አሽከርነትህ መላው የአማራ ህዝብ በቃኝ ብሎሃል ።ትግሉ የጥቂት ግለሰቦች ብቻ አይደለም ፤የመላው አማራ ህዝብ ትግል ከሆነ ውሎ አድሯል ። በመሆኑም በግፍ እስር ላይ የሚገኙ ልጆቻችን በአስቸኳይ እንድትፈታ እናሳስባለን። ማሳሰቢያ፦ ወንድሞቻችን በ30/10/15 ዓ.ም በከተማው ፍርድቤት ይቀርባሉ፤ ብልፅግና/ብአዴን የገማው እና የአማራ ጉዳይ የሚመለከተው ሁሉ፣ በሰዓቱ ችሎት ላይ እንዲገኝ ተጋብዟል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply